አርቲስት ታማኝ በየነ እና ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ፅጌ ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች እና የቀድሞ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር ዘመቱ።
ፖለቲከኛ ነዓምን ዘለቀ እና ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳም ወደ ግንባር ከዘመቱት መካከል ይገኙበታል።
በኢትዮጵያ ያጋጠመውን የህልውና ዘመቻ በተለያየ መንገድ ከፊት ሆነው ሲታገሉ የነበሩ አርቲስቶች እና የቀድሞ ሠራዊት የጦር አመራሮች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ወደ ግንባር መዝመትን ተከትሎ እነሱም እንደሚዘምቱ ከዚህ ቀደም ቃል ገብተው ነበር።
በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የህልውና አደጋ ለመመከት ዛሬ ወደ ግንባር መዝመታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
ሕዳር 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ)