“በጠላት መትረየስና ዲሽቃ የታሰረን ምሽግ እንደ ቀትር እባብ ተሽሎክሉኬ የቦምብ ናዳ አወረድኩባቸው፣ በየምሽጉ የነበሩት የጠላት ተዋጊዎችም የነበራቸው እድል የአሞራ ሲሳይ መኾን ብቻ ነበር” ምክትል ሳጅን አየለ ግርማ

November 25, 2021

ደባርቅ፡ ሕዳር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
በሰሜን ጎንደር ዞን በተከዜ ግንባር በተለያየ አካባቢ ወረራ የፈጸመውን አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኀይል እንዳይመለስ አድርገው መቅበር እንደቻሉ የአማራ ልዩ ኀይል አባሉ ምክትል ሳጅን አየለ ግርማ ነግሮናል። በጠላት መትረየስና ዲሽቃ የታሰረን ምሽግ እንደ ቀትር እባብ ተሽሎክሉኬ የቦምብ ናዳ አወረድኩባቸው፣ በየምሽጉ የነበሩት የጠላት ተዋጊዎችም የነበራቸው እድል የአሞራ ሲሳይ መኾን ብቻ ነበርብሏል ምክትል ሳጅን አየለ።

ምክትል ሳጅን አየለ ግርማ በጭና ላይ በነበረው አውደ ውጊያ ጠላትን እንደ ቅጠል በማርገፍ የሀገሩን ክብር ከፍ ማድረግ የቻለ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። ምክትል ሳጅን አየለ ግርማ የተሰጠውን ወታደራዊ ስልጠና በተግባር በማዋል የተመረቀበትን ተቋም ያስጠራ ቆራጥ ታጋይና አታጋይም ነው።

በነበረው አውደ ውጊያ ልበ ሙሉና በሳል አመራር ሲሰጥ የነበረ ቆራጥ የልዩ ኀይል አባል ነው፤ ምክትል ሳጅን አየለ ጠላት ባለበት እንዲቀበር መሪው ብቻ ሳይኾን የአከባቢው ማኅበረሰብ ርብርብና ተጋድሎም የሚያስደንቅ እንደነበረ ነው የነገረን።

ቦምቦችን በጠላት ላይ ለማዝነብ እየተሳብኩ ስሄድ በቀኝ በኩል የነበረው ጠላት ጥቃት ሊፈጽም ሲሞክር ቆፍጣናው መሪዬ ግንባሩን በመምታት ተደፍቶ እንዲቀር ስላደረገው ተግባሬን ሙሉ በሙሉ አሳክቼያለሁበማለት ይመራው ለነበረው አዋጊ ያለውን አክብሮትና አድናቆት ገልጿል።

በተከዜ ግንባር የሚገኘው የአማራ ልዩ ኀይል በጠላት ላይ ዳግም ታሪክ ለመሥራት በትጥቅ፣ በሞራልና በቁሳቁስ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መኾኑን ያስረዳው ምክትል ሳጅን አየለ የአማራ ሕዝብ ከጎናቸው እስከተሰለፈ ድረስ ምንም አይነት ችግር እንደማይገጥማቸው አረጋግጧል። የተራረፉትን የጠላት አባላት ዳግም ወደ አፈር በማዋሀድ የአማራን ክብር በማስጠበቅ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እናስጠብቃለን፣ ይኽን ለማድረግም ዝግጁ ነንብሏል።

ደባርቅን ለመውረር ቋምጦ የነበረው ጠላት ከፍተኛ የሰው ኀይል ቢያሰልፍም፣ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመኾን ሙሉ በሙሉ ወደ ለመደው መቃብር መሸኘቱን ምክትል ሳጅን አየለ ተናግሯል። በወቅቱ ጠላት ኹሉም ብርጌዶች ሲያልቁበት በአዲስ ቢተካም ለመግደል አልሰለቸንም ነው ያለው። በዚህ ግንባር ጠላት መጠነ ሠፊ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ስለደረሰበት አካባቢውን ዳግም እንዳይመኝ አድርጎታልም ነው ያለው።

አኹን ላይ ደግሞ በጭናና አካባቢው ከነበረው ድል የበለጠ ጀብድ ለመፈጸም ዝግጁ ነንያለው ሳጅን አየለ ባካበተው የውጊያ ልምድ ጠላትን ዳግም ለመቀጥቀጥ ቁርጠኛ መኾኑን ገልጿል። ኹሉም የብርጌዱ የአማራ ልዩ ኀይል አባላት እኛም የጀግኖችን ጀብድ መድገም አለብንበማለት እየተዘጋጁ ነው። አኩሪ ጀብድ ለመፈጸም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ተገቢውን ስልጠና በመውሰድ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀዋልብሏል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ፋኖ፣ ሚሊሻና ሕዝባዊ ሠራዊቱ ኹሉ በአንድነት የተሰለፉት ጠላትን እንደ ቅጠል ለማርገፍ መኾኑን ያስረዳው ምክትል ሳጅን አየለ የቁሳቁስ አቅርቦትም ኾነ የመደጋገፍ ትብብሩ ጠንካራ እንደሆነ ተናግሯል። ኹሉም የወገን ኀይል የአደረጃጀት እንጂ የዓላማ ልዩነት እንደሌላቸው ነው ያስገነዘበው። ጠላት በሚደመሰስበት ሁኔታ ላይ የኹሉም አደረጃጀት አባላትና አመራር ምክክር እንደሚያደርጉና መረጃን እንደሚለዋወጡም አመላክቷል።

ሻምበል ፍታለው ሙሉ፣ ምክትል ሳጅን አየለ ግርማ ስለሠራው ጀብድ እንዳሉት ምክትል ሳጅን አየለ በጭና በነበረው ትግል የጠላትን ምሽግ ማፍረስ ብቻ ሳይኾን የጠላትን መሳሪያ ማርኳል፣ የጠላትን አሰላለፍ በመረዳት ከፍተኛ ኪሳራ እንዲደርስበት አድርጓል ብለዋል። ምክትል ሳጅን አየለ በተለይ በጭናና በአካባቢው ታግሎ በማታገል የጠላትን ሞራል መስበር ችሏልያሉት ሻምበል ፍታለው የተዋጣለት ጀግና መኾኑንም መስክረዋል።

የአማራ ልዩ ኀይል ክፍለ ጦር በርካታ ጀብድ የፈጸሙ ጀግኖች እንዳሉትም ሻምበሉ ጠቁመዋል። ሌሎችም ጓዶች አርአያ ለመኾን የሚያስችላቸው ሥራ እየሠሩ መኾኑን የተናገሩት ሻምበል ፍታለው ጀብድ የፈጸሙ ጀግኖች ሊመሰገኑና ሊበረታቱ ይገባልም ብለዋል። ይሁን እንጂ ኹሉም የአማራ ልዩ ኀይል አባላት የአማራን ሕዝብ አደራ በመቀበል ጠላትን ለማጥፋት ጠንክረው ይሠራሉ ነው ያሉት።

ዘጋቢ:-ቡሩክ ተሾመከተከዜ ግንባር

#ተነሳ!!

#መሪህን ተከተል!!

#ሀገርህን አድን!!

#ነፃነትህን አትስጥ !!

#አካባቢህን ጠብቅ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ቀይ መስመር፡-የሥራና ክህሎት ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል – የመሪዎች ዘመቻ ከፖለቲካ እስከ ጦር ግንባር

Next Story

“በሰላም የኢትዮጵያ ብልጽግና ሚረጋገጥበትን መንገድ መስራት ብቻ ነው ምፈለገው… ተላላኪ መንግስ ኢትዮጵያ ውስጥ አይፈጠርም።” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

Go toTop