እግሬ አውጪኝ ብሎ ከግንባር እየፈረጠጠ የነበረውን የመከላከያ ሠራዊት – ዘመድኩን_በቀለ

November 1, 2021
እግሬ አውጪኝ ብሎ ከግንባር እየፈረጠጠ የነበረውን የመከላከያ ሠራዊት መካነ ሰላም ከተማ ላይ መንገድ ዘግተው ከሸሸህ ሽሽ፣ መሸሽ መብትህ ነው። ነገርግን የሃገር ሃብት የሆነውን መሳሪያህን አውልቀህ ስጠን ያሉትን የመካነ ሰላም ወጣቶች ረሽኖ የተዘጋውን መንገድ አስከፍቶ በዐባይ አቋርጦ ጎጃም ጥንታዊቷ መርጡለ ማርያም ከተማ የገባው የሃገር መከላከያ ሠራዊት እንደ መካነ ሰላሙ ገድለኸን አታልፋትም በማለት የበላይ ዘለቀ ልጆች በዚህ መልክ መንገድ ዘግተው ከፈርጣጩ መከላከያ ጋር ሙግት ገጥመው ይተጋተጉ ይዘዋል።
… ታያላችሁ ቱ ምንአለ በሉኝ አሁን ብአዴን ይደውልና የአካባቢዊን ካድሬ አዝዞ መንገድ የዘጋውን ረፍርፈኸው እለፍ ይለውና ያሳልፋቸዋል። ከምር ዐማራ እኮ ነው። መካነ ሰላም ላይ ወንድሙን ገድሎበት መጥቶ መርጦ ለማርያም ላይ በሬ አርዶ ያበላዋል። ብትገድለው፣ ብታርደው፣ ብትቀጠቅጠው ሁሉን የመቻል ትከሻ የታደለ። አይ ዐማራ ታድሎ። ብቻ መጨረሻውን ተከታትዬ አሳውቃችኋለሁ። የበላይ ዘለቀ ልጆች እንደ ትግሬ ልጆች ትንሽ ደፈር ያሉ ይመስላል። ለማንኛውም እኔ አያገባኝም። የጥርስ ህመሜ እኮ ነው እንዲህ የሚያስለፈልፈኝ።
ዘመድኩን_በቀለ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

“በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

Next Story

የጎጃም አማራ እግዚአብሔር ይወድሀል ብአዴን ያለ ትጥቅ ሊያሳርድህ ቢያሴርም እግዚአብሔር ቤትህ ድረስ ያመጣልህን እያስወለቅህ ታጠቅና አርበኛ ፋኖ ሁን

Go toTop