ለፋሽስት ወያኔ የውስጥ መረጃ በማቅረብ አማራን እያስጠቃ ያለው “ብአዴን” ነው!!!!!
የአብኑ የሱፍ ኢብራሒም በተወለደበት ደሴ ከተማ ውስጥ ባረፉበት ሆቴልና በሚጓዙበት መኪና ላይ ከትግራይ የመጡ ወራሪዎች ሶስት ጊዜ መድፍ ተኩሰው እንደሳቷቸው ነግሮናል። ይህ የሚያሳየው የፋሽስት ወያኔ አንበጣ ሠራዊት የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ የሚያደርገውን ስምሪት ብቻ ሳይሆን ግለሰቦች የት ቦታ እንደሚያርፉና ምን አይነት መኪና እንደሚያሽከረክሩ ሳይቀር ያውቃሉ፤ መረጃው አላቸው ማለት ነው። ፋሽስት ወያኔ ይህን ሁሉ ሚስጥራዊ መረጃ ከተራና ከተርታ ግለሰቦች ሊያገኝ አይችልም። በኔ እምነት የፋሽስት ወያኔ ታማኝ የመረጃ ምንጮችና አስተኳሾች የአማራ ርግማኖች የሆኑት ነውረኞቹ ብአዴኖች ናቸው። ፋሽስት ወያኔን ደብረ ታቦር ድረስ እየመራ የወሰዳቸው የብአዴኑ ሹም፤ የምዕራብ ደንብያው የደኅንነት ኃላፊ መሆኑን መዘንጋት አያስፈልግም። ፋሽስት ወያኔ ከኮረም እስከ ደሴ ድረስ የግፍ ወረራ ያካሄደው በዋናነት ከእንደምዕራብ ደንብያው የደኅንነት ኃላፊ አይነት የብአዴን ሰዎች በሚያገኘው ሚስጥራዊ መረጃና ሴራ እየታገዘ ነው። ስለዚህ የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽ የሆኑ ብአዴኖች ከጥቅም ውጭ ሆነው ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎው እስካሄደ ድረስ በብአዴን አዝማችነት የሚካሄደው ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎ ከጠላት ጋር ተሰልፎ ጠላትን ለማሸነፍ እንደመሞከር አይነት ጅልነት ነው። ባጭሩ የብአዴን የሆነው ነገር ሁሉ የኅልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ ታግዶ ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ በመከላከያው፣ በልዩ ኃይሉ፣ በሚሊሻውና በፋኖው የተቀናጀ ስምሪት ይመራ።