“የኢትዮጵያ መንግስት ጥሩ ሆኖ እንዳይታይ የሽብር ቡድኑ አባላት ሰብአዊ ድጋፉ ለትግራይ ህዝብ እንዳይዳረስ አድርገውታል”

September 24, 2021
ታዋቂዋ ኢትዮ አሜሪካዊት ትግራዋይ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ፣

22

መስከረም 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) መንግስት የወሰደውን ሕግ የማስከበርና የሕልውና ዘመቻ በመተቸት ለአሸባሪው ህውሓት ጠበቃ የነበሩ ታዋቂ ትግራዋይ ጋዜጠኞች እውነትን ወደ መወገን እየመጡ መሆናቸው እየታየ ይገኛል።

የሕግ ማስከበር ዘመቻውን በመተቸት ለአሸባሪው ህወሓት ጠበቃ የነበሩ ጋዜጠኞች እውነትን ወደ መወገን እየመጡ ነው።

በተለያዩ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ዘጋቢ በመሆንና በአሁኑ ወቅት ደግሞ በሲቢኤስ የዜና መረጃ መረብ በመስራት ላይ የምትገኘው ታዋቂዋ ኢትዮ አሜሪካዊት ትግራዋይ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ አሸባሪው ህወሓት የትግራይን ህዝብ ለስልጣን ጥቅሙ ብሎ እየተጠቀመበት እንደሆነ በትዊተር ገጿ አመላክታለች።

የኢትዮጵያ መንግስት ጥሩ ሆኖ እንዳይታይ የሽብር ቡድኑ አባላት ሰብአዊ ድጋፉ ለትግራይ ህዝብ እንዳይዳረስ አድርገውታል” ስትል አሸባሪው ቡድን ለስልጣኑ ሲል በትግራይ ህዝብ ላይ እያደረሰ የሚገኘውን መከራ አመልክታለች።

ጋዜጠኛዋ በቅርቡ በለቀቀቻቸው ጽሑፎች “የኢትዮጵያ መንግስት በተናጠል ያወጀውን ተኩስ አቁም አሸባሪው ህወሓት ለምን ጣሰ? ወደ አማራና አፋር ክልሎችስ ወረራ በማካሄድ ንጹሃንን ለመግደልና ውድመቶችን ለመፈጸም ለምን ፈለገ?” ስትል ጠይቃለች።

የተመድ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ባለፈው ሳምንት ወደ ትግራይ የእርዳታ እህል ጭነው ከተላኩት 466 ተሽከርካሪዎች የተመለሱት 38ቱ ብቻ ናቸው ያለውን ሪፖርት አጽንዖት በመስጠት የሽብር ቡድኑ በትግራይ ህዝብ ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ግፍ አውግዛለች።

እርዳታ ጭነው የገቡ መኪናዎች አለመመለስ ለምን ሆነ ይህ ለህዝቡ እርዳታው እንዳይሰራጭ አያደርግም ወይ?” በማለት ነው ቡድኑ እየፈጸመ የሚገኘውን ነገር የኮነነችው።

አሸባሪው ቡድን በከፈተው ጦርነት “ምን ያህል ህጻናት እስኪያልቁ ነው የሚጠበቀው” በማለትም ሔርሜላ ትጠይቃለች።

ባለፉት አስር ወራት በትግራይ ተከሰተ የተባለውና የሰማሁት ነገር አይመጣጠንም አሁንም ነገሮችን በተለየ አይን በመመልከት ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ እናምጣ ብላለች።

ወቅቱ በውጭ የምንገኝ ደጋፊዎች ቆም ብለን ራሳችንን የምናይበትና ከጭፍን ድጋፍ ወጥተን መፍትሔ የምናመጣበት ጊዜ ሊሆን ይገባል ስትል ነው ያመለከተችው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

mekonen 2
Previous Story

ኒቼና የኦሾ ፍልስፍና እንደገና መጠናት ያለበት ነው ፡፡ የቀደመ ሃሰብ ያዘ ነውና ! – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

242920449 6474461325927387 2611980491318147400 n
Next Story

ለቸኮለ! ቅዳሜ መስከረም 15/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

Go toTop