ሽብርተኛው ህወሃት አሁን ላይ የገጠመውን ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስና የሎጅስቲኪ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ አማራጮችን ለመጠቀም ጥረት በማድረግ ላይ ነው።
ሱዳን በሚገኙ ስደተኞች ሽፋን ሊካሄድ የተዘጋጀው የገቢ ማስገኛ የሙዚቃ ዝግጅትም ገንዘቡን ማን ያድርስ በሚለው ጉዳይ ከፍተኛ አመራሮቹና አርቲስቶቹ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጭምርውየውስጥ አዋቂ ምንጮች አስታውቀዋል።
አሸባሪው ህወሓት የሽብር ቡድኑ በዛሬው ዕለት (ሀምሌ23 ቀን 2013 ዓ.ም) በሱዳን ለሚገኙ የትግራይ ስደተኞች የገቢ ማስባሰቢያ መርሃ ግብር በሚል ሽፋን ከተለያዩ ዓለማት በመጡ የጁንታው ደጋፊ ሙዚቀኞች አማካኝነት በካርቱም ቡሪ በተባለ አካባቢ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ከምሽቱ አንድ ሰአት ጀምሮ ፕሮግራም ለማካሄድ ተዘጋጅቷል፡፡
በዚህም ፕሮግራም ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹና ተባባሪዎቹ ይገኛሉ ብሎም አልሟል፡፡
ከዝግጅቱም በሰው እስክ 10ሺህ የሱዳን ፓውንድ እንደሚሰበሰብ ይጠበቃል ያሉት ምንጮቻችን፤ ለትግራይ ህዝብና እና እናቶች ደንታ የሌላቸው የስግብግቡ ጁንታው ከፍተኛ አመራሮች የለመዱትን የጫካውን አይነት ጭካኔ በመፈፀም ከዝግጅቱ የሚገኘውን የገንዘብ ገቢ ወደ ግል ኪሳቸው ለማስገባት ቋምጠዋል ብለዋል።
የሙዚቀኞች ቡድን የሚሰበሰበውን ገንዘብ እኛ እራሳችን ለስደተኞች በአካል ተገኝተን እናደርሳልን በሚል የጁንታውን ከፍተኛ አመራሮች እየሞገቱ ሲሆን፤ የሽብርተኛው አመራሮች በበኩላቸው ገንዘቡን ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል ባላቸው ፍላጎት ከሙዚቀኞች ቡድን ጋር ግብግብ ፈጥረዋል፡፡
በመሆኑም የሽብር ቡድኑ በትግራይ ህዝብ ስም የሚገኝን ገንዘብ ለጦርነት ዓላማው እየተጠቀመበት ሲሆን፤ በአስከፊ ችግርና መከራ ውስጥ ያለው የትግራይ ህዝብ የአሸባሪውን የህወሃት ቡድንን እኩይ ድርጊት ሊቃወመውና ተው ሊለው ይገባል ካሉ በኃላ፤ በተጨማሪም በሱዳን እየታየ ያለው ውስጣዊ የሰላም እጦትና ችግር ላይ ተመስርቶ ለጁንታው ጥላቻ ያላቸው ማንነታቸው የማይታወቅ አካላት ጥቃት ሊፈጽሙ እንደሚችሉም ጭምር ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ያላቸውን ስጋት አሳውቀዋል፡፡
(ኢ.ፕ.ድ)