ኢትዮጵያን አፍርሶ እንጨቷን ለመሞቅ የሚደረገው ሩጫ ከማራቶን ወደ 5 ሺ ሜትር ተቀይሯል።
በዚህ ፈታኝ ጊዜ ለአገር አንድነት በጋራ እንደመቆም፣ ” ጊዚያዊ መንግስት አቋቁሜያለሁ” እያሉ በአመጽ ጫና ለመፍጠር መሞከር በታሪክ ፊት ያስጠይቃል። ይህም ጊዜ ያልፋል። ኢትዮጵያም ትቀጥላለች።
እስከዛሬ ያልተመለሰልኝ አንድ እንቆቅልሽ አለ። እባካችሁ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እርዱኝ። በህወሃት ሲሳደዱ የነበሩ ሰዎች አሳዳጃቸውን መልሰው የሚናፍቁበት ሚስጢር ምንድን ነው?