ያመኑት ፈረስ ከፈሩት ፈረስ – መስፍን አረጋ

January 5, 2020

እያረጋጋ በመለሳለስ
ያመኑት ፈረስ ጥሎ በደንደስ
ይረጋግጣል እስከሚጨርስ፡፡

በሌላ በኩል የፈሩት ፈረስ
እንቅስቃሴው ሳያሰኝ ደስ
ስለሚደረግ ልጓም እንዲነክስ፣
በመንሸራተት በጎን ከግላስ
ከመውደቅ የከፋ ከቆመ አጋሰስ
የባሰ ጉዳት እምብዛም አይደርስ፡፡

ከኦነግ ፈረሶች ዐብይና ጃዋር
ጦቢያን የሚገላት ጥሎ ከኦዳ ሥር፣
ሳይሆን ያልተገራው የአሩሲው ስናር
ያጋሮው ጮሌ ነው ያመነው ሙሉ አገር፡፡

ስለዚህ ጦቢያዊ አማራው በተለይ
ጦቢያን ጥሎ እንዳይገል አሙለጨላጩ ዐብይ፣
ለጃዋር ማስካካት ሳትሰጠው ጉዳይ
ሙሉ ትኩረትህን አድርግ በጮሌው ላይ፡፡

መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com

 

Previous Story

ሰው ገና በእናቱ መሐፀን ሣለ ህሊናውከፈጣሪው ጋር ተሳሥሯል።ይህ ትሥሥርም የፈጣሪ በየነ መረብ ወይም GOD network ይባላል – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Next Story

ፍራሽ አዳሽ -5- ተስፋሁን ከበደ – ውሃ ውስጥ ሆኖ የሚያልበው አሳ ጦቢያ ግጥምን

Go toTop