፩) መግቢያ:
ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መፈጠሪያ ቦታ ለመሆኗ በሳይንስም ሆነ በሃይማኖት የተረጋገጠ ሃቅ ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአርኪዮሎጂ ቁፋሮ በሚገኙ የሰው ቅሪተ አካላትና በ DNA ምርመራ መሠረት የሚሰጡ ሳይንሳዊ ትንታኔዎች የሚያመላክቱት ጥንታዊ ሰዎች የሀገራችንን ስምጥ ሽለቆ መነሻ በማድረግ በአካባቢያቸው የሚገኝ የተፈጥሮ ልምላሜንና የወንዞችን ተፋሰስ በመከተል በቅድሚያ በዙሪያቸው በኢትዮጵያ ምድርና በአፍሪካ በቀጣይም ሀገራችንን በየብስ እና ቀይ ባህርን አቋርጠው ወደ ተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እንደተሰራጩ ይገልፃሉ። በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ኤደንን ከከበቧት አራት ወንዞች መሃል አንዱ ከኢትዮጵያ የሚመነጨው የግዮን (አባይ) ወንዝ መሆኑን ይነግረናል። ፈጣሪ አዳምንና ሄዋንን ከምድር አፈር ከፈጠርራቸው በኋላ በዚሁ በኤደን ውስጥ እንዲኖሩና ዘራቸውን እንዲተኩ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉዋት ብሎ እንደባረካቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። በመሆኑም በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ልጆች ሲወለዱ፣
፪) የኢትዮጵያ ህዝብ ፍልሰትና መቀላቀል (ባጭሩ)
በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ ጊዜ የተደረጉ የህዝብ ፍልሰትና ስርጭት በሦስት አቅጣጫ የተደረጉ ነበሩ። አንደኛው ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ ውጭ የተደረገ ፍልሰት፣ ሁለተኛው ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገ፣ ሶስተኛው ደግሞ ከአንደኛው የኢትዮጵያ ክፍል ወደ ሌላኛው የኢትዮጵያ ክፍል የተደረገ የሃገር ውስጥ ፍልሰት ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያ በአንድ በኩል የሰው ልጅ መገኛ በሌላ በኩል ደግሞ በርካታ ሰዎች ተሰደው በመምጣት የኖሩባትና ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የተቀላቀሉባት ናት። ቀደምት አባቶቻችን በዚህች ምድር ላይ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ፣ በዓየር ንብረት መዛባት እና በተለያዩ ምክንያቶች ተሰደዋል፣ ከአንዱ የሃገራችን ጫፍ ወደሌላው ጫፍ ተመላልሰዋል፣ በሂደቱም ህዝቦች ከህዝቦች ጋር ተደባልቀዋል። ከሃገር ውስጥ ፍልሰት እንደ ምሳሌ ለማንሳት ያህል 1) ዮዲት ጉዲት በአክሱም መንግስት ላይ የፈጸመችው ውድምት ምክንያት የንጉሳን ቤተሰቦች ጭምሮ በከተማው በተለያየ ሞያና ስራ ተሰማርተው የነበሩ በርካታ የማህበረሰቡ ክፍሎች ወደ መሃል እና ደቡብ ኢትዮጵያ መሰደዳቸው፣ 2) በኦቶማን ቱርክ ይታገዝ የነበረው ግራኝ አህመድ (ኢማም አህመድ ቢን ኢብራሂም አልጋዚ) ከሃረር ( እና ከዘይላ) ተነስቶ በወቅቱ በነበረው በኢትዮጵያ የክርስቲያን መንግስት፣ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና በምዕመኑ ላይ ከ 14 ዓመት ላላነሰ ጊዜ የፈጸመው ሰፊ ወረራ፣ ውድመት፣ ቃጠሎ፣ ግድያና ዝርፊያ ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የህዝብ ፍልሰት፣ ከዛም በመቀጠል 3) ቦረና እና ባሬንቱ የሚባሉ ጥንታዊ የኦሮሞ አርብቶ አደር ነገዶች (Primitive Oromo pastoral tribes) ቀድመው ይኖሩበት ከነበረው አካባቢ በሁለት አቅጣጫ ፈልሰው በመምጣት “በባሊ” (ባሌ) እና “መደ ወላቦ” በተባሉ አካባቢዎች መጥተው ሰፈሩ። ከጊዜ በኋላ የህዝቡና የከብቱ ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ የመሬት ጥበት ችግር ስላጋጠማቸው ከጎሳ እስከ ነገድ ድረስ ቅንጅት በመፍጠር ገዳ በሚባል ባህል በመደራጀት ጎረቤቶቻቸው ላይ ጭካኔ የተሞላበት ሁኔታ በመንጋ ወረራ በመፈፀም ነዋሪውን ህዝብ ከኖረበት ቀዬው በማፈናቀል፣ በመግደል ወይም ማርኮ በማወረም (በሞጋሳ ባህል) በመሬቱ ላይ ስፈሩበት። ይህ ድርጊት ከተፈፀመ ዘመናት ያስቆጠረና ባልሰለጠነ ኋላ ቀር ጊዜ የተከሰተ በመሆኑ በታሪክነቱ መዝግቦና ትምህርት ወስዶ ከማለፍ ውጭ በዚህ ዘመን ለጸብና ክርክር ምክንያት መሆን የለበትም። እዚህ ላይ ማንሳት የምፈልገው ሌላው ነገር ግን በጥንት ዘመን የነበረው ጥንታዊ የኦሮሞ ማህበረሰብ (Primitive Oromo pastoral tribes) እና አሁን በዘመናችን በሚገኘው የኦሮሞ ህዝብ (Contemporary Oromo) መሃል የባህል፣ የአኗኗር፣ የእምነት፣ የአስተሳሰ
ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገን ፍልሰት ስንመለከት ደግሞ ከሺህ ዘመን በፊት ቀይ ባህርን አቋርጠው ከኢትዮጵያ ምድር ተነስተው ወደተለያዩ የዓለማችን ክፍል ተሰደው ከነበሩት ጥንታዊ ነገዶች ውስጥ በሄዱበት ቦታ አዲስ ባህልና ቋንቋ አዳብረው ክርበርካታ ትውልድ በኋላ በወጡበት ባል አል ማንዳብ (Bal-al-Mandab) ተብሎ በሚጠራው በቀይ ባህር ሰርጥ በኩል ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ምድር ፈልሰው በመምጣት ከነባሩ ህዝብ ጋር ተቀላቀሉ፣ ከነዚህም ውስጥ ሳባውያን ይጠቀሳሉ። ሳባውያን ከክርስቶስ ልደት በፊት 1000 ዓመታት አካባቢ የኤደንን ባህረ ሰላጤን በማቋረጥ ወደ ሃገራችን መፍለሳቸው ይታወቃል።
፫) “Barbarians at the Gate”
ሮማውያን “Barbarians at the Gate” የሚል አገላለፁ ነበራቸው። አባባሉ የቆየ ታሪክ ያለው ሲሆን በህግና ስርዓት የማይመሩ፣ ያልሰለጠኑ፣ ባዕዳን ማህበረሰቦች (Barbarians) የሮማን ከተማ በመንጋ በመውረር በከተማው ላይ ያስከተሉትን ውድመትና በነዋሪው ህዝብ ላይ የፈጸሙትን እልቂት ለመግለጽ የተጠቀሙበት አገላለጽ (Metaphor) ነው። በተለይ በ8ኛው ክፍለ ዘመን ቫይኪንግ/ ኖርማንስ (Vikings/ Normans) የተባሉ በእስካንዴኔቪያን (Scandinavian) ሃገሮች ማለትም በኖርዌይ፣ በስዊድንና በዴንማርክ ይኖሩ የነበሩ ጥንታዊ ህዝቦችን ነበሩ። እነዚህ ህዝቦች አሣ በማጥመድ፣ በአነስተኛ ግብርና፣
አውሮፓውያን በጥቅሉ “Barbarian” (Foreigners/ ባዕዳን) ብለው የሚጠሯቸው እነዚህ ማህበረሰቦች
፬) አዲስ አበባ እንደ ኖርማንዲ (Normandy)
የቫይኪንግ/ ኖርማንስ የወረራ ታሪክ የራይን ወንዝን በእግርና በፈረስ በማቋረጥ በሮም መንግስትና ህዝብ ላይ በፈፀሙት ውድመትና ወረራ ብቻ አያበቃም። ነገር ግን ከእስካንዴኔቪያ አካባቢ በመነሳት በቡድን
ታላቋን ሮምን በጎሳ ደርጃ የሚያስቡ ያልሰለጠኑ በመንጋ የሚያስቡ ቫይኪንጎች እንዳወደሟት ሁሉ በዚህ ባለንበት በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ፊደል ቆጥረናል የሚሉ የኦሮሞ ብሔረተኞች ሳይቀሩ ሁሉ ነገር “ኬኛ” በሚል “ክፉ የዘረኝነት መንፈስ” ተለክፈው ለንደል ላይ እንደ ቃልቻ ሟርት ኢትዮጵያን አፈራርሰን የኦሮሚያ ሪፕብሊክ እንመሰርታለን በማለት ፎከሩ። በሃገር ውስጥ ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ባለቤት ኦሮሞ ነው፣ ሊላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ተከራይ መኖር ብቻ ነው፣ የራሱንም እድል በራሱ ለመወሰን ሰው መሆኑ በቂ ሆኖ ሳለ የአዲስ አበባ ህዝብ ብሔረሰብ ስላልሆነ መብት የለውም በማለት ቁጥሩ ወደ 6 ሚሊዮን የሚጠጋ የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ተሳለቁ። በእንደመር ሂሳብ ተቅለስለሰው ሃገር ውስጥ ገብተው ሲያበቁ ሃገራችንንና ከተማችን አዲስ አበባን በማፍረስ፣ ህዝቧን በመበተን ሃገር አልባ፣ ባይተዋር ለማድረግ፣ ያልደከሙበትንና ያልገነቡትን ከተማ ሊወርሱ ቀን ከሌሊት እየዶለቱ ይገኛሉ። ሰባተኛ ንጉስ ነኝ ያለን ጠቅላይ ሚኒስትራችን የፈረንሳዩ ንጉስ ቻርለስ 3ኛ “ኖርማንዲንን/ Normandy” ቫይኪንጎች ሃገሩን ሁሉ ከሚያጠፉት አሳልፎ እንደሰጥቸው እንደመር በሚል ውል በሌለው ቃላት ህዝቡን እያጃጃለ ለዘመናችን ቫይኪንግ ለሆኑት ኦነጋውያንና ጃዋራውያን ሃገራችንን እና ህዝባችንን ለባርነት አሳልፎ ለመስጠት እያደባ ይገኛል።
አዲስ አበባን አይደለም መላው ኢትዮጵያን ይታደጋሉ ብለን ተስፋ አድርገንባቸው የነበሩት አዲስ አበባ ሲገቡ ጭራቸውን ቆልፈው በሰባተኛው ንጉስ እግር ስር ተንበርክከው ፍርፋሪ ለቃሚ ሆኑ። ከኔ በላይ እሱን ስሙት አሉን። ስለሆነም ነፃነታችንን ማስከበር ያለብን እኛ እንጂ ሌላ ሰው ሊሆን አይገባውም። ስለዚህ የአዲስ አበባ ህዝብ ሆይ እራስህን ከመዋጥና ከመጥፋት አድን፣ በሃገርህ ላይ ሁለተኛ ዜጋ ሳያደርጉህ፣ የአፓርታይድ ሰለባ ስዳትሆን፣ በሃገርህ ላይ ስደተኛ፣ የበዪ ተመልካች ሳያደርጉህ፣ ተጫውተህ ካደክባት፣ አግብተህ ከወለድክባት፣ ወግ ማዕረግ ካየህባት፣ እናት አባቶችህ ዋጋ ከፍለው ካስረከቡህ ከሃገርህ ላይ እንደ እንጉዳይ ከሥርህ ነቅለው ሳይጥሉህ ለመብትህና ለነጻነትህ ተነስ። ሮም በወራሪዎች ጠፍታለች አንተም ለመብትህ ካልታገልክ አዲስ አበባም ተመሳሳይ እድል የማያጋጥማት ምክንያት የለም። ለነጻነትህ ተነስ! ተደራጅ! ታገል! “Freedom is not free”–//–
ደረጀ ተፈራ