ህወሓት የመጨረሻ እድልዋን ለመሞከር ማሰር ትቀጥላለች፣ እስሩ ከመፈፀሙ በፊት ህወሓት እነ ኪዳነ ከዓረና እንዲወጡ በሰጠችው መመርያ ዓረና ከለቀቁ እንሆን ሁለት ቀናቶች ተቆጥረዋል። የትግራይ ህዝብ ከዚህ ቦሃላ ለህወሓት ፊት እንደማይሰጥ የገባቸው ህወሓቶች ሁሉም አምባገነን እንደሚያደርገው፣ በህዝቡ ላይ ፍራቻ ለመፍጠር መጀመርያ አብርሃ ደስታ እና ዓምዶም ለማሰር ወስናለች። ሚኪ ተስፋየ ትናንትና ማታ በፖሊስ ታስረዋል። አመት ብአል ጠብቀው በቅዳሜ ቀን አስረውታል። ሃይለኪሮስ ውቅሮ ውስጥ ታስሮ ተፈተዋል። .
.
መቀሌ ከአዲስ አበባ በመጡ የደህንነት ሰዎች መሞላትዋ የታወቀ ቢሆንም፣ ካሁን ቦሃላ ወደ አራት ኪሎ መመለስ እንደማይችሉ ስለገባቸው፣ ትግራይ መሽጎ የትግራይን ህዝብ እያስፈራሩ መግዛት ብቸኛው አማራጭ የሆነባት ህወሓት፣ ወጣቱን ለማስፈራት ከነ አብርሃ ደስታ እና ዓምዶም እንዲማር ሁለቱንም ለማሰር ወስናለች። ህወሓቶች እንደ ቦኮሓራም ራሳችን የምገዛው ህዝብ እና ክልል አለን ብለው ስለሚያስቡ፣ እነ አብርሃ ከታሰሩ ቦሃላ ማእከላዊ ወይንም ቃሊቲ የሚወስድዋቸውም እንዳይመስላቹ፣ መቀሌ የሚገኘው ሓለዋ ወያኔ ውስጥ ነው የሚያስርዋቸው።.
.
የትግራይ ልዩ ሃይል፣ እስካሁን ድረስ በ 5 ዙር ሰልጥኖ በወጣ ፖሊስት ትግራይን በተለይ ደግሞ መቀሌን ለመጠበቅ ወስናለች። ትግራይ በተለይ መቀሌ ካሁን ቦሃላ የህወሓቶች አራት ኪሎ ሆና ትቀጥላለች፣ ህወሓትን የተቃወመ በሙሉ እጣው ዱላ እና እስራት ነው። የትግራይ ልዩ ሃይል ህዝቡን እንዲያሸብር ተብሎ፣ ምርጫ 97 አዲስ አበባ ውስጥ ሲዞሩ እንደ ነበሩ ኮማንዶዎች፣ የትግራይ ልዩ ሃይልም፣ በየ ጎዳናው በብዛት መዞር ጀምረዋል። .
.
እንግዲህ የትግራይ ህዝብ በገዛ ልጆቹ ይበልጥ የሚጨቆንበት፣ የሚገረፍበት እና የሚታሰርበት ጊዜ ላይ ይገኛል፣ በደርግ ጊዜ መቀሌ ውስጥ ሲገድል ሲቀጠቅጥ የነበረው መ/አለቃ ደስታ ታደሰ ዘንድሮ በነ አቦይ ስብሓት ተተክቶ የትግራይ ወጣቶች መደብደብ ማሰር እና መግደል ሊጀምሩ ነው። ህወሓት ትግርኛ ተናጋሪ ደርግ መሆንዋን አስመስክራለች። የ ፸ እንደርታው ጀግና ጠበቃ እንዳይቀጥር ውክልና እንዳይሰጥ መታወቅያው ነጥቀው፣ የህግ ከለላ የማግኘት ህገመንግስታዊ መብቱን ጥሰውታል፣ ህገመንግስቱ ተጥሰዋል ብለው ሰልፍ የሚወጡ ህወሓቶች በድጋሚ ህገመንግስቱን ራሳቸው ሲጥሱት አይተናል። .
.
ዛሬም አብርሃ ደስታን እና ዓምዶም ማሰር ትችሉ ይሆናል፣ ነገ ግን እንደ ዛሬ እንዳይመስላቹ፣ ጋድፊ ሳዳም አልበሽር ሄደዋል፣ ይህ በትግራይ እንደሚመጣ ግን ለአፍታ እንካን እንዳት ዘነጉት፣ የዛሬ አርባ ሰባት አመት ደደቢት ስትገቡ፣ ደርግ ዴሞክራስያዊ አይደልም ብላቹ ደርግ ይወድቃል ብላቹን ነግራቹን ነበር፣ደርግም ወደቀ፣ እናንተም እንደምትወድቁ ዛሬ በእርግጠኝነት ልነግራቹ እፈልጋለሁኝ። አወዳደቃቹ እንደ ሳዳም እንዳይሆን ግን እሰጋለሁኝ፣ ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ስራ እና ፍትሕ ያጣ የትግራይ ህዝብ በተለይ ወጣቱ አንድ ቀን ይበላችዋል። የጊዜ ጉዳይ ነው!!!