በሁመራ ኦምሀጁር በኩል ያለው የንግድ እንቅስቃሴ መዘጋቱ ተነገረ፡፡ ኤርትሪያን ፕሬስ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው መንገዱን በአጣና የዘጋው የትግይ ክልል መንግስት ነው፡፡ ይህ የሁመራና ኦምሀጁር መንገድ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያና ኤርትራን የሚያገናኝ ዋናው መስመር እንደሆነ ይታወቃል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=9_PNwyW18Qg&lc=z232dvlz4rjojzig504t1aokggiygcg51eftmpfbzcukrk0h00410
በሁመራ ያሉ አንድ ምንጭ ለኤርትሪያን ፕሬስ እንደተናገሩት በዚያ መንገድ ሲጓዙ ከነበሩትና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችንና ጤፍ ጭነው የነበሩትን ከባድ መኪናዎች በማስቆም ትግርኛ ተናጋሪ ካልሆኑት በተለይ ከኦሮሞና አማራ ተወላጅ የተባሉት ላይ እየተመረጡ ላይ ዘረፋ ፈፅመዋል፡
ይህ ድርጊት የተፈፀመውም የክልሉ መንግስት ዋና መቀመጫ ከሆነው መቀሌ በተላለፈ የከፍተኛ ባለስልጣናት ትእዛዝ መሆኑን የዜና ምንጩ አስረድቷል፡፡
ይህ በሁመራ ወደ ኦምሀጁር የሚወስደው መንገድ ለ20 አመታት ተዘግቶ ከቆየ በኋላ የተከፈው በቅርቡ ሁለቱ አገራት ከታረቁ ወዲህ መሆኑ ይታወቃል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=9_PNwyW18Qg&lc=z232dvlz4rjojzig504t1aokggiygcg51eftmpfbzcukrk0h00410