በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተጠረጠሩት 19 ኤርትራዊያን በዛሬው እለት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የኬንያ ጋዜጦች ዘገቡ፡፡ እንደመረጃው ከሆነ ተጠርጣሪዎቹ በፕራዶ መኪና የኬንያን ሞያሌ ከተማ ሊያቋርጡ ሲሉ የተያዙት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=9K1EwuewSOA
ከኢትዮጵያ ተነስተው የኬንያን ድንበር ሲያቋርጡ የተያዙት እነዚህ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ክስ ስለቀረበባቸው ጠፍተው እየሄዱ መሆኑን ገልፀው እቅዳቸውም ዩኔንኤችሲአር ጥገኝነት መጠየቅ እንደነበር ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ዋስትና ሳይፈቅድላቸው ጉዳዩን ለሚቀጥለው ወር ቀጥሮታል፡፡