ስራው የቆመውን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማስቀጠል የኢትዮጵያ መንግስት ስራውን ሙሉ በሙሉ ለቻይናዊያን መስጠቱ ታወቀ፡፡ የግድቡን ግንባታ በተመለከተ ከሁለት የቻይና ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈፀመ፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=SvwytfrDZTg&t=73s
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በትላንትናው እለት የተፈራረመው ስምምነት40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ ሲጂጂሲ CGGC የተባለው የቻይናው ኩባንያ ግድቡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2020 ስራ እንዲጀምር የሚያስችሉ ግንባታዎችንና ሌሎች ስራዎችን እንደሚያከናውን ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብርሀም በላይ በስምምነቱ ወቅት ሲናገሩ ‹‹ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመጣመር ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል›› ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የግድቡን የኤሌክትሪካል፣ ሜካኒካልና ስትራክቸራል ስራዎችን እንዲያከናውን በ113 ሚሊዮን ዶላር ቮይዝ ሀይድሮ ሻንጋይ ከተሰኘው የቻይና ተቋም ጋር ስምምነት መደገሩ ይታወሳል፡፡