Español

The title is "Le Bon Usage".

አቶ በረከት ስምኦን በነጠላ ጫማ ፍርድ ቤት ቀረቡ! 

January 25, 2019

ወህኒ ቤት እንዲወርዱም ትእዛዝ ተላልፏል

 በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ጥንቅሹ በዛሬው እለት በባህር ዳር ፍርድ ቤት ቀርበው፣ ችሎቱ ጉዳያቸውን ለየካቲት 1 ቀን 2011 ከቀጠረ በኋላ ወደማረሚያ ቤት እንዲወርዱ አዟል፡፡

 

ጉዳዩን የተመለከተው የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አቶ በረከት ስምኦን ወደፍርድ ቤቱ በፖሊስ ታጅበው የደረሱት ጠቆር ያለ ሱሪና ኮትና ከውስጥ ነጭ ሸሚዝ ለብሰው ሲሆን ነጠላ ጫማ አድርገው ነበር፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=RvScL9Cy1vM&t=1064s

 

ፍርድ ቤቱ በቅድሚያ ስለራሳቸው እንዲያብራሩ በጠየቀበት ወቅትም አቶ በረከት እድሜያቸው 62፣ ባለትዳር፣ የ3 ልጆች አባትና አሁን ስራ እንደሌላቸው ሲናገሩ አቶ ታደሰ ካሳ በበኩላቸው እድሜያቸው 53፣ ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የተከሰሱበትን የክስ ማመልከቻ ለእያንዳንዳቸው እንዲደርስ ካደረገ በኋላ ምላሽ እንዲሰጡ ጠየቀ፡፡ ተጠርጣሪዎቹም ድርጊቱን እንዳልፈፀሙ መልስ ከሰጡ በኋላ በፖሊስ ጣቢያ የደረሰባቸውን ጫና አብራርተዋል፡፡

አቶ በረከት ሲናገሩ ‹‹ከዚህ በፊት በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች በደቦ ፍርድ እየተሰጠኝ ነው፡፡ ትናንትና በቁጥጥር ስር ባለሁበት ፖሊስ ጣቢያ ሌባ፣ ዘራፊ፣ ነፍሰ ገዳይ እየተባልሁ ተሰድቤያለሁ፣ ስለሆነም የክልሉ መንግስት ክብራችን ሊያስጠብቅ ይገባል›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹ቤተሰቦቼ የፍርድ ሂደቱን እንዳያዩ ተከልክለዋል፣ ምግብ አልተሰጠንም›› የሚሉ ቅሬታዎችን አቅርበዋል፡፡ በትላንትናው እለት ለምሳሌ ምሳ የተሰጣቸው ከቀኑ 10 ሰአት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

አቶ ታደሰ ካሳ በበኩላቸው ተመሳሳይ ስድብ እንደደረሰባቸውና የህግ የበላይነት እንዲከበር ጠይቀዋል፡፡

አቶ በረከት መንግስት የሚያውቀው የደም መርጋትና የልብ ህመም እንዳለባቸው፣ አቶ ታደሰም እንደዚሁ የአስም በሽተኛና የልብ ህመም እንዳለባቸው ለፍርድ ቤቱ አብራርተዋል፡፡ በመሆኑም በርካታ መድሀኒቶች አንደሚወስዱ ቤተሰቦቻቸው እያዘጋጁ የሚያቀርቡላቸውን ሀኪም ያዘዘው ምግብ በተወሰነ ሰዓት እንደሚመገቡ ጠቁመው ስለሆነም ጉዳያችን ቤተሰቦቻችን ባሉበት በአዲስ አበባ ይታይልን የሚል ጥያቄ ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡

እንደዚሁም የተጠረጠሩበት ወንጀል በእስር ቤት ሆኖ ለመከራከር የሚያስችል መሰረት ስለሌለው በውጭ ሆነን እንከራከር ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አቶ በረከት በተለይ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ከታገዱ በኋላ ወደ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ አንዲሁም በአገር ውስጥ በስም መጥቀስ ባይፈልጉም እርሳቸው “የሽፍቶች መደበቂያ” ተብሎ ይጠራል ወዳሉት አካባቢ ድረስ መሄዳቸውንና ጉዳያቸውን በራስ መተማመን ከእስር ውጭ ሆነው መከራከር እንደሚችሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡ አቃቤ ህግ በሰጠው ምላሽ ተጠርጣሪዎች ይመሩት የነበረው ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ለአንድ የውጭ ኩባንያ በ90 ሚሊዮን ዶላር መሸጡን ጠቁሞ ነገር ግን ፋብሪካው የተሸጠበት ገንዘብ በጥረት ውስጥም ሆነ በዳሽን ቢራ ካምፓኒ ውስጥ አይገኝም ብሏል፡፡

 ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችም ያልተሰበሰቡ በመሆኑ ግለሰቦቹን ከእስር መልቀቅ ከነበራቸው ስልጣን አንፃር መረጃ ያጠፋሉ የሚል ስጋት ስላለ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት አንዲከታተሉ ጠይቋል፡፡

ጉዳያቸውም በባሕር ዳር የሚታየው የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈፀመው በአማራ ክልል በመሆኑ እንደሆነና ወደ አዲስ አበባ ይዛወርልኝ የሚለው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም ብሏል አቃቤ ህግ፡፡ አመጋገባቸውን በተመለከተ አስካሁን የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አቅም በፈቀደ መጠን ሲያቀርብላቸው መቆየቱን ጠቅሶ ካሁን በኋላ ግን ቤተሰቦቻቸው እንዲያቅርቡ አመልክቷል፡፡ እንደዚሁም ለተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የ14 ቀናት አንዲፈቀድለት አቃቤ ህግ ጠይቋል፡፡

የግራ ቀኙን አስተያየት ካዳመጠ በኋላ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በዚሁም መሰረት ግለሰቦቹ ከነበራቸው ከፍተኛ ስልጣን አንፃር መረጃ ሊያጠፉ ይችላሉ ከሚል እሳቤ ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ፣ የተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት የተፈፀመው በአማራ ክልል በመሆኑ ጉዳያቸው በባህር ዳር እንዲታይ ወሰኗል፡፡

ቤተሰቦቻቸውም በማንኛውም የፍርድ ሂደት ወቅት እየቀረቡ እንደማንኛውም ሰው ሂደቱን እንዲከታተሉ፣ አቃቤ ህግ የጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተግባራዊ እንዲሆንና የካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ፣ ፖሊስም አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግላቸው በማለት ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ወስኗል።

አቶ በረከት ወደ ፍርድ ቤት ሲገቡም ሲወጡም ከውጭ የነበረው በርካታ ህዝብ በ ዕል;ታ ደስታውን ሲገልጽ የነበረ ሲሆን ሌባ ሞላጫ እያሉ የሚዘምሩም የሚሉም ነበሩ::

Previous Story

ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ…

Next Story

ድሬዳዋ ዛሬም ሳትረጋጋ ዋለች

Zehabesha | Ethiopian Latest News, Top Analysis & Best Articles <h1 style="text-align:center">tHE HABESHA Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win</h1><title> <title><h2 style="text-align:left">Get the Best Scholarly Articles and Analysis on ZeHabesha</h2><title> <title><h3 style="text-align:right">Zehabesha Ethiopian News</h3><title> <title><h4 style="text-align:justify">Ethiopian Lates News</h4><title> <meta name="keywords" content="Ethiopian News, Ethiopia News, Ethiopian News Today, Top Stories, The Habesha, Latest News, Ethiopia, Breaking News, zehabesha, zehabesha Amharic News, The Habesha News, Headlines, borkena. bbc amharic, repoter, mereja, Ethiopian News provider"> <!-- Google Tag Manager --> <script>(function(w,d,s,l,i){w[l]=w[l]||[];w[l].push({'gtm.start': new Date().getTime(),event:'gtm.js'});var f=d.getElementsByTagName(s)[0], j=d.createElement(s),dl=l!='dataLayer'?'&l='+l:'';j.async=true;j.src= 'https://www.googletagmanager.com/gtm.js?id='+i+dl;f.parentNode.insertBefore(j,f); })(window,document,'script','dataLayer','GTM-5WDL6STX');</script> <!-- End Google Tag Manager --> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=G-W9E3TWE2TL"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'G-W9E3TWE2TL'); </script> <meta name="msvalidate.01" content="4781C31A916C7AB883D8AF1F4F3BFC49" /> <link rel="icon" href="/path/to/favicon.ico"> <link rel="icon" type="image/png" href="/thehabesha.com/favicon-96x96.png" sizes="96x96" /> <link rel="icon" type="image/svg+xml" href="/thehabesha.com/favicon.svg" /> <link rel="shortcut icon" href="/thehabesha.com/favicon.ico" /> <link rel="apple-touch-icon" sizes="180x180" href="/thehabesha.com/apple-touch-icon.png" /> <link rel="manifest" href="/thehabesha.com/site.webmanifest" /> <meta name="seobility" content="48b995a16caf3ab9d546a000c18b65d3"> <main> <!-- Main content of your page goes here --> </main> <script type="text/javascript" src="//cdn.rlets.com/capture_configs/d2b/aac/e54/1fc4f7ea32cf1e1d818a0f2.js" async="async"></script> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=TAG_ID"></script> <script src="https://www.googleoptimize.com/optimize.js?id=OPT-M8Z33GL"></script> <meta name="google-site-verification" content="Lf_65x5pXGn-W1TA8CsfJi-53aAyIKdfVyM_QkwpvgY" /> <head> <title>Ethiopian Latest News: Top Analysis and the best Articles<title> <script defer data-domain="thehabesha.com/mEUHSv" src="https://api.publytics.net/js/script.manual.min.js"></script> <script> window.publytics = window.publytics || function() { (window.publytics.q = window.publytics.q || []).push(arguments) }; publytics('pageview'); </script> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=UA-215686007-9"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'UA-215686007-9'); </script> <script async src="https://pagead2.googlesyndication.com/pagead/js/adsbygoogle.js?client=ca-pub-9091845805741569" crossorigin="anonymous"></script> <script async custom-element="amp-ad" src="https://cdn.ampproject.org/v0/amp-ad-0.1.js"></script> <title>Zehabesha Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win