ከኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ ወለቴ ቀበሌ 03 ልዩ ቦታው አጃንባ ከሚባለው አካባቢ ተፈናቅለው አዲስ አበባ ፋኑኤል ቤተክርስቲያን ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ቤተክርስቲያኗን ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=epx_GOJUaUQ
በረራ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ይህ ትእዛዝ የተላለፈባቸው ከቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ነው፡፡ እነዚህ ተፈናቃዮች ለጋዜጣው ሲናገሩ ‹‹ከዛሬ ነገ ችግራችን ይቀረፋል ብለን ብንጠብቅም ወደ ሌላ ችግር እየገባን ነው›› ብለዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ ችግራቸውን እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ቢያሳውቁም ምንም ምላሽ እንዳላገኙም ተናግረዋል፡፡ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ የሖኑት መምህር ያሬድ በላይነህ በበኩላቸው ‹‹ይህን ትእዛዝ ያስተላለፍነው ተፈናቃዮቹ ህገ ወጥ በመሆናቸው፣ በመጀመሪያም ወደቤተክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ሲገቡ ፈቃድ ባለመጠየቃቸው እንዲሁም ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ከተለያዩ አካላት ትእዛዝ ስለተሰጠ ነው›› በማለት ለጋዜጣው ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ተፈናቃዮች የሰበታ ከተማ አስተዳደር ህገ ወጥ ግንባታ አድርጋችኋል በሚል ህዳር 4 ቀን 2011 ለቀው እንዲወጡ በተላለፈ ትእዛዝ የተፈናቀሉ መሆናቸውን በረራ አስታውሷል፡፡