ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በአሜሪካና አውሮፓ ተጉዘው ከኢትዮጵያውያን ጋር ባደረጉት ውይይት ዲያስፖራው በቀን $1 እንዲያዋጣ ከጠየቁ ወዲህ ከ3 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ገንዘብ ያዋጡት 2800 ብቻ እንደሆኑ አመለከቱ።
እስካሁን የተገኘውም $507,094 መሆኑን ከማሰባሰቢያው ድረገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁም ተገልጿል::
ዲያስፖራው በድጋሚ አሁንም ይህንን ጥሪ ተቀብሎ በአንድ አንድ ዶላር የማዋጣቱን ተግባር እንዲቀጥል የተጠየቀ ሲሆን በአንጻሩም ዶ/ር አብይ የሾሙት ቦርድም በዋሽንተን ዲሲ ብቻ ስብሰባ አድርጎ ክመበተን ይልቅ በተለያዩ ስቴቶች እየተዟዟረ ሕዝብን የማንቃት ሥራውን እንዲያከናውን ሌሎች የገቢ ማሰባሰቢያና የግንዛቤ መስጪያ ፕሮግራሞችን እንዲዘረጋ ሕዝብ በተለያየ መንገድ እየጠየቀ ነው::
በሌላ በኩል ዶ/ር አብይ ዛሬ “ግዴታየን እወጣለሁ፤ መብቴንም እጠይቃለሁ” በሚል መሪ ቃል የገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀው ሃገራዊ የገቢ ንቅናቄ ዛሬ በይፋ በተጀመረበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የግብር ገቢ ለአገር እድገትና ስልጣኔ ዋነኛ መሰረት እንደሆነ ገልፀው ግብር ከፋዮች ለሀገርና ለወገን ያላቸውን ፍቅር ለማሳየት የግብር አከፋፈል ሀላፊነትና ስነልቦና ማጎልበት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል::
ግብርን የሚያጭበረብሩ ዜጎችን እንደ ብልጥ መመልከት መቆም ያለበት ድርጊት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደዚህ ዓይነት ድርጊቶችን ልናወግዛቸው ይገባልም yalut dor abye በአግባቡ ግብር የሚከፍሉትን መንግስትንና ልጆቹን እንደሚወድ ዜጋ እንመለከታቸዋለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለንግድ ፍቃድ መነገድ፣ ሙስና፣ በግብር ማጭበርበር እና ሌሎች ህገወጥ የሆኑ አካሄዶች የዘርፉ ማነቆዎች መሆናቸውን አንስተው ይህ ሊቆም ይገባልም ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር ግብር ለ ኢንቨስትመንት ያለውን አስተዋጽዖ አብራርተዋል፡፡ የንቅናቄው ዐላማ ኢትዮጵያን በ2017 ወደ ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ ያለመ ነው፡፡ ለዚህ ማስፈጸሚያም እስከ 2012 መጨረሻ 2.3 ትሪሊዮን ብር ከግብር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን 75 በመቶው ከታክስ ገቢ የሚሰበሰብ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ 60 በመቶው መሠረታዊ አግልግሎቶችን ለማስፋፋት ይውላል፡፡ ባለፉት ጥቂት ዐመታት ከሀገራዊ ምርት አንጻር የታክስ ገቢ ምጣኔ በተከታታይ ቀንሷል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=s58PBvypjSM