የጋምቤላው ፕሬዚደንት ‹‹ከዶክተር አብይ ጋር ተደምረናል፡፡›› አሉ!

November 27, 2018

አዲሱ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የጋሕአዴን ሊቀመንበር ኡሞድ ኡጁሉ ከመንግታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ‹‹ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጋር ተደምረናል፡፡›› ሲሉ ተናገሩ፡፡ ጨምረውም ‹‹ለዚህ ማሳያው ባለፈው ሰፊ ጊዜ ተወስዶ በግምገማ አማካይነት የተደረገው ለውጥ በራሱ እማኝ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም በክልሉም የተለያዩ ድጋፎች እየተሰጡ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ ቁልፍ ችግሮች መለየታቸውን የተናገሩት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በአዲስ አበባ ለ14 ቀናት በተካሄደ ግምገማ የፀጥታ ችግርና የልማት ፕሮጀክቶች መጓተት በክልሉ መስተዋላቸውን ገልፀዋል፡፡ ‹‹በክልሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ሙስና መንሰራፋት የክልሉን ህዝቦችና ወጣቶች ተጠቃሚነት ጎድቶታል፡፡›› ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ በክልሉ አልሚ ካልሆኑ ባለሀብቶች መሬት እየተነጠቀ ወደ መንግሥት የሚመለስበት ሥራ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚህ መሰረት ንብረትነቱ የሼህ መሀመድ አል አሙዲ የሆነው የሳዑዲ ስታር ድርጅት ከያዘው አስር ሺ ሄክታር መሬት አምስት ሺ ሄክታር ተቀንሶ ወደ መንግሥት እንዲመለስ በማድረግ የክልሉን ወጣቶች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደታቀደ ገልፀዋል፡፡ አቶ ኡሙድ በዚሁ ቃለ ምልልስ ‹‹ወደ አገር ውስጥ ከገቡ ፓርቲዎች መካከል የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄና የጋምቤላ ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ይገኙበታል፡፡

እስከአሁን ግን ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጣቸው እውቅና የለም፡፡›› ብለዋል፡፡ በቀጣይነት ክልሉ ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ሰላምና ፀጥታ እንዲመለስ በትጋት እንደሚሰራም አስረድተዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=kk-bdasg-qA&t=158s

Previous Story

ዶ/ር አብይ ተፎካካሪ ፓርቲዎች 3 ወይም 4 እንዲሆኑ ጥሪ አቀረቡ

Next Story

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ

Go toTop