ፕሮፌሰር መረራ ‹‹የጠመንጃ ፖለቲካ ማብቃት አለበት›› አሉ

November 11, 2018

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የጠመንጃ ፖለቲካ መብቃት እንዳለበት አሳሰቡ፡፡ ፕሮፌሰሩ ሲናገሩ ‹‹ይህ የጠመንጃ ፖለቲካ መብቃት አለበት፡፡ ደርግ 17 አመት በጠመንጃ ገዛ፣ የአንድ ትውልድ ልጆችን ገድሎ መጨረሻ ራሱም ተዋረደ፡፡ ኢህአዲግም በ27 አመታት ያንኑ ሞከረ፡፡ ህዝብን ዘላለም በጠመንጃ መግዛት አትችልም፡፡ ህዝብን የምትመራበት የተሸለ ልማትንና ብልፅግናን የምታመጣበት የተሻለ ህዝባዊ አስተዳደር የምታሰፍንበት መንገዶች አሉ፡፡ ውድድሩ ካለ እዚህ ላይ መወዳደር ነው፡፤ ይህንን ሁላችንም ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባል›› ብለዋል፡፡
ፕ/ር መረራ ይህን የተናገሩት ትላንት በአዲስ አበባ ለንባብ የበቃው ‹አብይ ጉዳይ› መፅሄት ላይ ነበር፡፡ በዚሁ መፅሄት በኢትዮጵያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ፖለቲካችንን ማስተካከል እንደሆነ ያስረዱት ፕሮፌሰሩ፣ ፖለቲካው ከተስተካከለ ሀቀኛ የፍትህ ስርአት በኢትዮጵያ ምድር እንደሚፈጠር ተስፋቸውን ጠቁመዋል፡፡ አሁን በኢህአዲግ ውስጥ የተፈጠረውን ለውጥ በተመለከተ ሲያብራሩም ‹‹መሰረታዊ ለውጥን በሚያመጣ ደረጃ አልተከለሰም፡፡ ነገር ግን ተነካክቷል፡፡ ብዙ ቦታ የፍትህ ስርአቱም ሆነ ደህንነቱም ሚዲያውም ብዙ ተነክተዋል፡፡ ግን እነዚህ ሁሉ ተጠቃለው መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ብሎ መደምደም ይቸግራል›› ብለዋል፡፡
አባባላቸውን በምሳሌ አጣቅሰው በመንግስትና በተቃዋሚዎች መሀከል ብሄራዊ ስምምነት እንደሌለ፣ ብሄራዊ መግባባት እንዳልተፈጠረ፣ ሁሉም በራሱ መንገድ እየሰራ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹መሰረታዊ በሆኑ የአገሪቱ ጉዳዮችላ ይ በተፎካካሪ እና በመንግስት መሀከል ምንም ስምምነት የለም›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህም በጣም ወሳኝ የሆኑት ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው ኢትዮጵያን ወደተፈለገው አቅጣጫ የሚወስዱ ጉዳዮች ገና እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=f9ZDJjIZNkI

Previous Story

በሌብነትና በሌሎች ወንጀሎች የሚፈለጉ የጦር መኮንኖች ታፈሱ | ልዩ ግብረ ኃይል ወደ መቀሌ አቀና

Next Story

ለ18 አመታት ያህል በትግራይ ክልል ታስሮ የቆየው ካሳሁን ሲሳይ ‹‹በትግራይ የሚታሰር አማራ የከፋ ግፍ ይፈፀምበታል›› አለ

Go toTop