ከወራት በፊት ከአጋዚ ጦር ጋር የሚመሳሰል ‘ማበል ግብረሃይል’ የተባለ በዶ/ር ዓብይ አህመድ አማካኝነት እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን ከዚህ ከማበል ግብረሃይል አንዱ ሻምበል ወደ ቤተመንግስት ከነጠመንጃው መሄዱ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው የውስጥ መረጃ ይጠቁማል::
ከማበል ግብረሃይል በኮለኔል አያናው መስፍን ከበላይ ሆኖ የሚያዘውና ማዕረጋቸው ለጊዜው ማዕረጋቸው ያልተገለጸ ሞሲሳ እና በምክትሉ ፈቃዱ የሚመራው ሻምበል ጦር ወደ ቤተመንግስት በመሄዱ ከበስተጀርባው ያለው የደመወዝ ጥያቄ ሳይሆን ሌላ ነው በሚል ሦስቱም የክፍተኛ የጦር መኮንኖች ተጠርጥረው መታሰራቸውን የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል::
በቡራዩ የተከሰተውን ሁኔታ ለማርገብ ከአዋሳ የመጡት እነዚሁ ሞሲሳ እና ፈቃዱ የሚመሩት ሻምበል ጉዳይ አሁንም መነጋገሪያነቱ የቀጠለ ሲሆን በወታደሮቹ መሰረታዊ የደመወዝ ጥያቄ ጀርባ ሌሎች የተሴሩ ነገሮች ናቸው በሚል መከላከያው አሁንም እየታመሰ መሆኑ ታውቋል::
ለጊዜው የሶስቱ ከፍተኛ ጦር መኮንኖች ስም የመታሰራቸው ስም ይፋ ይሁን እንጂ በርካታ ሃላፊዎች እየታሰሩና
እየተገመገሙ ይገኛሉ::
_
https://www.youtube.com/watch?v=d1wWzuTMu2s