አሰቃቂ ሞት በሊቢያ ሰሃራ – ከዲጄ ቶም (ቪድዮ)

October 8, 2013

ከሱዳን በረሃ እስከ ሊቢያና ሜድትራኒያን ባህር ድረስ ያለውን ስቃይ ካለፉ ሰዎች መካከል አንዱ ዲጄ ቶም ነው። ዲጄ ቶም አሰቃቂውን ጉዞ እንዲህ ይተርከዋል። ዲጄ ቶም በፌስቡክ ገጹ ያካፈለውን ቪድዮ ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ በሚስማማ መልኩ አስተናግዳዋለች። ዴጄ ቶም ምርጥ ሥራ በመስራቱ ዘ-ሐበሻ ያላትን አድናቆት በዚህ አጋጣሚ ትገልጻለች።
ከዲጄ ቶም
በመጀመርያ ለዚች ቀን ላበቃኝ እግዚኣብሔር ይመስገን በእርግጥ ያለፈውን ስቃይ ሳስበው ለዚች ቀን እደርሳለው የሚል ተስፋ ኣልነበረኝም በቦታው ሆነህ ስታየው በታም ከባድ ነው በዚ ሰዓት ህሊናዬ ላይ ድቅን የሚልብኝ ኣንድ በጣም የምወደው ጓደኛዬ ነው። ሁለታችንም ኣንድ ዓይነት ፍልስፍና ነበረን እሱም “ጉዞዬ ረዥም ፣ ተስፋዬ ሩቅ ፣ችግሬ ብዙ ነው” የሚል ሁለታችንም በጣም ከምንወደው መጽሃፍ ከዣንቫልዣ (ምንዱባን) የወሰድነው ኣባባል ነበር። እሱ ወደ ሩቅ ተጉዞዋል እኔ ግን አለሁ።

Previous Story

መንገድ ወድቆ አየሁት – ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

Next Story

Sport: “የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድንን እናከብራለን፤ ግን እናሸንፋቸዋለን” – ሳላዲን ሰኢድ

Go toTop