ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ መስከረም 26 ቀን 2006 ፕሮግራም
<<...መረጃውን በአንድ ቀን አይደለም ፎቶ ኪፒ ያደረኩት። ወይም የአንድ ሳምንት ስራ አይደለም።...የመጀመሪያዋን መረጃ ስለሱ ያለኝን በእርግጠንነት መሬት ላይ ሊያስረግጠኝ የሚያስችለውን ካየሁ በሁዋላ ብሽቀት ነው የተሰማኝ። ያ ብሽቀቴ ግን እንዳይታወቅ ካወቀብኝ ደግሞ በእጁ ያሉ ቦርሳው አጭቆ የሚዞራቸው መረጃዎቹን...>>
አክቲቪስት አለማየሁ መሰለ የቀድሞ የቅንጅት አመራር አንዱ ስለ ደራሲ ተስፋዬ ገ/አብ ሰሞኑን ይፋ በሆነው ጽሁፍ መረጃዎቹን እንዴት እንደሰበሰበ ለህብር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ
<<...የአሜሪካ መንግስት መዘጋት በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ የሚያመጣው ተጨማሪ ጣጣ አለ...>> ስለ አሜሪካ መንግስት መዘጋት ከባለሙያ ጋር ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)
ልዩ ዘገባ ከሊቢያ ተነስተው ጣሊያን ባህር ዳርቻ ህይወታቸው ስላለፈ ኤርትራውያን፣ሶማሊያውያንና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሰቃቂ አሟሟት
(ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን)
ዜናዎቻችን
– ፕ/ት ግርማን ይተኩዋቸዋል ተብለው ግምት ከተሸጣቸው ደ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ/አምባሳደር መሀመድ አሊ እና ብርሃነ ደሬሳ ይገኙበታል
– የጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ እህት እስረኛዋን እንዳትጠይቃት በመደረጉ ምሬቷን ገለጸች
– የሙስሊሞቹ ሰላማዊ ትግል እንደሚቀጥል ተገለጸ
– ሰማያዊ ፓርቲ በአምስት ወራት ለተቃጠሉት ስመንት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ መንግስትን ማብራሪያ ጠየቀ
– የኢትዮጵያ ብ/ቡድን የግብጽ አቻውን የወዳጅነት ግብዣ ውድቅ አደረገ
– የአሜሪካ ኮማንዶ ድንገት በሶማሊያ ላይ በወሰደው ጥቃት የአልሸባብ ባለስልጣንን አጠቃ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን