በአንድ ቀን በአዲስ አበባ፣ በወልቃይትና ባህርዳር የሕወሓትና ብአዴን ንብረቶች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ

March 28, 2017

ከሙሉነህ ዮሐንስ

ቃጠሎ አንድ
አዲስ አበባ

ልዩ ስሙ ጃክሮስ በሚባል አካባቢ አ.አ ውስጥ በሚገኘው እጅግ ግዙፍ በሆነው የወያኔ ኤፈርት ሁሉን አቀፍ አስመጪና መላኪያ መጋዘን እና ፋብሪካ ክፍል በተቀነባበረ ሴራ በተለኮሰ እሳት በትንሹ እስከ 40 ሚሊዎን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ፡፡ በርካቶችን ለእስራት እየዳረገ ነው፡፡

ቃጠሎ ሁለት
ወልቃይት

440 ኩንታል ጥጥ ወልቃይት ላይ ተቃጠለ። ጥቃቱ የወያኔን የንግድ ጥቅሞች ላይ ጉዳት ለማድረስ ነው የሚሉ ዘገባዎች ወጥተዋል።

ቃጠሎ ሶስት
ባህር ዳር

አመልድ (እየተጣራ ነው) እየተቃጠለ ነው የሚል መረጃ አሁን መጣ። ይህም የወያኔ/ብአዴን ተቋም መሆኑ ነው።
እናም በወያኔ ላይ አዲስና የተቀነባበረ ጥቃት እየተፈፀመ ከሆነ መቆሚያ አይኖረውም። ምክንያቱም ጥቃቱን ለማድረስ መስዋእትነት አያስከፍልም:: ጉዳቱ ግን ከፍተኛ ነው። ወያኔ ደግሞ ገንዘብ በጣም ታፈቅራለች…ይህ ያንኮታኩታቸዋል…ወየው ለማረት ወየው ለኤፈርት…

በሌላ በኩል በባህርዳር የተከሰተውን ቃጠሎ ተከስቶ ከፍተኛ ተኩስ ማምሻውን እየተሰማ መሆኑን ከስፍራው የመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

ዝርዝር መረጃዎች እንደደረሱን እናቀርባለን

Previous Story

በመደብ ትግል የሚያምኑ በመደብ ትግል ይደመሰሳሉ – ሸንቁጥ አየለ

Next Story

ይበቃል ከአንግድህ …….የበላይ  ለመሆን

Go toTop