በደቡብ ኮርያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በዛሬው እለት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በ ሰውል ኣካሄዱ።

September 5, 2013
ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የማያባራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም በደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ጽ/ ቤት ፊት ለፊት ፕሬስ ኮንፈረንስ በማድረግ የኮርያ መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥር ተማጽነዋል። ለ ደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ፓርክ  ግን-ሄ ደብዳቤም ኣስገብተዋል።
ሰልፈኞቹ  ለደቡብ ኮርያ  UNHCR  ተወካይና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደብዳቤዎችን ያስገቡ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥሩ ተማጽነዋል።
ከሰልፈኞቹ መሃል ኣብዛኛዎቹ የዘማች ልጆች ሲሆኑ ባለፈው ጊዜ ለስልጠና መጥተው ገዢውን መንግስት በመቃወም ጥገኝነት መጠየቃቸው ኣይዘነጋም።
Previous Story

ኳሧ በእሳቸው እጅ ሣትሆን በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ነች።

Next Story

የሐምሌ ጨረቃ (ክፍል ሁለት) – አንዷለም አራጌ ከቃሊቲ ማጎሪያ የላከው መልዕክት እጃችን ደርሷል

Go toTop