ባለፈው ሳምንት የሸአብያ ሰራዊት ተከዜን ተሻግሮ ሰርጎ በመግባት ወደ ወልቃይት ሕሞራ በመውረር በህዝብና በጸጥታ ሀይሎች ጉዳት ለማድረስ ሞክሮ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የአከባቢ ምልሻዎች በከባድ የመከላከለ ውግያ በሸአብያ ሰርጎገቦች ሰራዊት ከባድ ማጥቃት እንዳደረሰና የተማረኩም እንዳሉም ከወደ ህሞራ የሚነገሩ አሉ ።
መንገስት ግን ባገር ያሉ ሰላማዊ ተቃዋሚ ሀይሎች በድህረ ገጽ ጻፋችሁ ፣በአመሪካ በጀርመን ሬድዮ ተናገራችሁ ተብለው በሚዲያ ስማቸው እያጠፉ ፣በከባድ እሱር ቤት እየተሰቃዪ ፣እንዳይሰበሰቡ ፣ለአባሎቻቸዏ እንዳይቀሰቅሱ ፣ የቁም እሱሮኞች ሆነው ። በአንጻሩ ሸአብያ በየቀኑ ፣በየሰአቱ በሰራዊታችንና በህዝባችን ጥቃት እያደረሰ መንግስት ለህዝብ መረጃ እንደስጠት ዝምታን በመምረጥ አንድ ቃልም ስለየሸአብያ ወንጀል ለመግለጽ አልቻለም ።ሚስጢሩ ምን ይሆናል የሚለው የህወሐት ኢህአደግ አንጋፋ መሪዎች ይመልሱት ። ጦርነቱ በተዋጊ አውሮከፕላኖች የታጀበ እንደነበር ይነገራል ።
ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ፣
14 -/3 /2009 ዓ ም
የሸአብያ ሰራዊት ተከዜን ተሻግሮ – ህወሐት ኢህአደግ የሸአብያ ወንጀል ለምን ይደብቃል? -ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ
አቶ አስገደ ገ/ስላሴ