ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በአመክሮ ከእስር ቤት አይፈታም

October 14, 2016

ታሪኩ ደሳለኝ

የዝዋይ እስር ቤት አስተዳዳር በተመስገን ደሳላኝ ላይ በፃፈው የአመክሮ መከልከያ ቢጫ ወረቀት ላይ ይህን አስፍሯል
1. የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፁሁፎች አሁን ሀገሬቷ ላለችብት ነገር ዋናውን አስተዋፆ ይወስዳሉ
(በነገራችን ላይ ይሄ የፍርድ ቤት ስራ እንጂ የእስር ቤቱ አስተዳደር ስራ አይደለም)
2. አመክሮ አለገመገም ብሏል
(የእስር ቤቱ አስተዳደሮች ተመስገንን ይሄን 20 ቀን ሙሉ አመክሮ እንዲገመገም ብንለምነው ብናስለምነው አመክሮ አልገመገምም ብሏል)
3. በእስር ቤቱ ውስጥ አድማና አማፅ ቀስቅሷል፣ እስረኞችን አደራጅቷል ተጨማሬ መብታችሁን ጠይቁ ብሏል
በሚሉ ምክኒያቶች ተመስገን ደሳለኝ ከእሰር ቤት እንደማፈታ ተነግሮናል፡፡

ተመስገን በእስር ቤቱ ውስጥ 2 ዓመታት ሲያሳልፍ ለአያሌ ጊዚያት ጭለማ ቤት፣ ቅጣት ቤት እና በቤተስብም በውዳጅም እንዳይጠየቅ ተደርጓል አንዲሁም ምንም አይነት ህክምና አንዳያገኝ ተክልክሏል እንዚህ ነገሮች ሲደረጉበት ግን በእስር ቤቱ ህግ መሰረት ስላጠፍክ ለዚህን ያሀል ጊዜ ቅጣት ቤት ትቆያለህ ወይም ለዚህን ያህል ጊዜ ማንም ሰው አይጠይቅም ተብሎ አልተከሰስም የፈለጉትን በሻቸው ሰዓት አደረጉበት እንጂ፡፡ እንግዲህ በእስር ቤት ቆይታው ምን አይነት ጥፋት አጠፋህ ተብሎ ያልተጠየቀ ያልተከሰስ ነበር፡፡ በመጨረሻ ሰዓት ማለት መስከረም 30/09 ዓ.ም ይህን አደርገሀል ብለው መፃፋቻ ግራ አጋቢ ነው፡፡
እንግዲህ እኛም ከዚህ በኋላ ለተጨማሬ 1 ዓመት የግፍ ግፍ ለሆነው እስር ወደ ዝዋይ እስር ቤት እንመላለሳልን፡፡ እውነት ነው የዝዋይ ጉዞዎ አድካሜ ነው ግን ተመስገን ለሀገሬ ስል እስከ ቀራኒዬ እጎዛለሁ ካለው ጋር ፈፅሞም አይገናኝም ለዚህ ነው ጉዞችን የኩራት አንጂ የህፍረት የማይሆነው፡፡

Previous Story

መንፈሳዊ ወኔና ስልጣን (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

Next Story

በባሕር ዳር 67 ሆቴሎች የባንክ ብድር መመለስ አንችልም ብለዋል

Go toTop