20 የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ከሕዝብ ጋር ተቀላቀሉ

September 12, 2016

ከሙሉቀን ተስፋው

ከአዲስ አበባ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ቦሌ አየር መንገድ ሕገ ወጥ የእጽ ዝውውር ላይ አንድ ሻለቃ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሃያ የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ክደው ባለፈው ሳምንት ከሕዝብ ጋር መቀላቀላቸው ታውቋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ አባላቱን ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸው በሕዝባቸው ላይ እየደረሰ ያለው መቆሚያ ያጣ ፍጅት ነው ተብሏል፡፡
በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሠራዊት የዐማራ ተወላጆች ተለይተው መሣሪያ እንዳይዙ እንዲደረግ ሀሳብ የቀረበ ቢሆንም ስምምነት ባለመኖሩ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ ሆኖም የዐማራ ተወላጆችን መሣሪያ ከሰጡ በኋላ ልዩ ክትትል እንደሚደረግባቸው የዐማራ ተወላጅ የሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት ገልጸዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ደግሞ የአዋሽ አካባቢ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ሌሎች ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ከድተው መሄዳቸው ታውቋል፡፡
ዝርዝር ጉዳዮችን በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል!!
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!

Previous Story

ድርድር አይሠራም! አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ

Next Story

የአማራ ክልል የወያኔ መቀበሪያ

Go toTop