የህብር ሬዲዮ ሰኔ 12 ቀን 2008 ፕሮግራም
እንኳን ለአባቶች ቀን አደረሳችሁ !
<… የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ለየራሳቸው የሚያደርጉትን ሩጫ በአንድ ላይ አስተባብረው ሰቶ በመቀበል ፖሊሲ በጋራ ለመታገልና ኢህአዴግን አስገድደው በቃህ ለማለት የሚችሉበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ ኢህአዴግንም ለሚቀልቡ ምዕራባውያን በአገሪቱ ስርዓቱ ባይኖር ሁኔታውን አረጋግቶ ለመምራት የሚችል አማራጭ መኖሩን ማሳየት ይቻላል ይህ ሳይሆን ግን እነሱን ብቻ መውቀሱ …ይሄ ስርዓት ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት ሕዝብን ከሕዝብ ለማጣላት ብዙ ሲሰራ ቆይቷል። ኦሮሞውና አፋሩን፣ኦሮሞውና ቤንሻንጉሉን፣ አማራው ላይ በጉራ ፈርዳ የተወሰደው ፣ኦሮሞውና ሶማሌውን ብዙ መጥቀስ ይቻላል የሻሸመኔውም የሰሞኑ ሁኔታ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ብዙ ዋጋ የሚያስከፍለን ነገር እንዳይመጣ ያሰጋል …> ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦፌኮ ሊቀመንበር በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<…የኢትዮ-ኤርትራ የመጀመሪያውን የጦርነትን ግጭት ተከትሎ በሰራዊቱ ውስጥ ብዙ ነገር ታይቷል። የሰራዊቱንም አመራር የተቆጣጠረው የህወሓት ዘረኛ ቡድን በጾረና ግንባር ያዘመተውን ለአገርህ ተዋጋ ተብሎ የተጠራውን የቀድሞ ሰራዊት ድል ካደረገ በሁዋላ ሙሉ ለሙሉ አባረውታል ወደ ግንባር የሌላውን ብሄር እየለዩ ለፈንጂ ረጋጭነት ያሰማሩ ነበር …ይሄ የሰሞኑ ከኤርትራ ጋር የተነሳው ግጭት በሶስቱ ግንባሮች በማድመ፣በጾረናና በቡሬ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ሰፍሮ ባለው ሰራዊት መካከል አልፎ አልፎ ከሚነሳው ግጭት ላቅ ያለው የህወሓት አመራር አጋጣሚውን ተጠቅሞ በኤርትራ ያሉ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች የፈጠሩበትን ስጋት ለማስወገድ ሲል የገባበት ጭምር ነው።ሕወሓት የሚያነሳው ጦርነት በምንም መንገድ ቢሆን የአገር ጦርነት … > ኮ/ል ደረሰ ተክሌ የሰራዊቱ የቀድሞ የጥናትና ምርምር ክፍል ሀላፊ በኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዲፕሎማቶች ኬኒያ ላይ ከሰሞኑ የድንበር ላይ ቁርቋሶ በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜያት በግንባር በመገናኘት ስለ ውስጣዊ እና አካባቢያዊ ችግሮቻቸው በተመለከተ ከርረ ያለ እና ከዲፕሎማቲክ ደረጃው የዘለለ የቃላት ልውውጥ አድረገዋል።ሁለቱ አምባሳዳሮች በምን ጉዳይ ላይ ተሰማሙ? ሰሞነኛውን ጦርነትንስ ማን ጀመረው? ለሚለው ጥያቄ ምላሻቸው ምንድን ነው? (ልዩ ጥንቀር)
<…የጎንደር ልማት ማህበር በሰሜን አሜሪካ እስካሁን ከሰላሳ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ተማሪዎች ስኮላር ሺፕ ሰጥቷል አሁን ተጨማሪ አስራ አምስት ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ ጥያቄ አቀረቡ ።ለዚህ ክተኛ የአቅም ችግር ገጥሞናል…ሁለት አማራጭ ነው አለን ወይ የተማሪዎቹን ቁጥር መቀነስ ወይ ተጨማሪዎቹን አለመቀበል። እነዚህን ከአስራ አንደኛና አስራሁለተኛ ክፍል የላቁና በመስፈርቱ ስፖንሰር የምናደርጋቸው ተማሪዎችን በጋራ እንድንረዳቸው ያስፈልጋል…> ዶ/ር ሙላቱ ውብነህ የማህበሩ የቦርድ ሊቀመንበር ለህብር ሬዲዮ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)
የእንግሊዝ ሕዝብ ከአውሮፓ ሕብረት አባልነት ለመውጣት ወይም አብሮ ለመዝለቅ ለሕዝበ ውሳኔ ምርጫ ተቀመጠዋል። ለመሆኑ በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ነዋሪዎች ምን ይላሉ? የዓለማችን መሪዎች ህዝበ ውሳኔውን በተመለከተ ምን አሰተያየት እየሰጡ ይገኛሉ? የተለያዩ አስተያየቶችን አካተናል የሕብር ራዴዮ ልዩ ዘግጅትን ያድምጡ
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
ሜጄር ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት(ጆቤ) የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራር የትግራይ ተወላጆች እርስት ሆኖ መቅረት የለበትም አሉ
ሳሞራን ሕዝብን ይቅርታ ይጠይቅ ብለዋል
የዓለም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች በታሪክ ታላቅ የተባለ ስብሰባ በግሪክ አካሄዱ | የሩሲያ ኦርቶዶምስ መሪዎች ራሳቸውን አገለሉ
የውጭው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲኖዶስ ለቅዱሳን አባቶች ሹመት ሰጠች
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከሰሞነኛው የጾረውና ግጭት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ኬኒያ ውስጥ በግንባር ተገናኝተው ተወዛገቡ
“አናሳው የትግራይ ወያኔው መንግስት ወደ ልቦናው እንደሚመለስ ተሰፋ አደርጋለሁ” የኤርትራው አምባሳደር በየነ ርእሶም
“በአገሩ አንምዳችም የህዝበ ወሳኔ ያላድረገ መንግስት እንዴት ስለ አናሳዎች መብት ሊናገር ይቻለዋል?”የኢትዮጵያው አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ዶ/ር መረራ ጉዲና ተቃዋሚዎች ስርዓቱን ማስገደድ የሚያስችል የጋራ ትግል እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ
በሻሸመኔ በስለት ሰባት የኦሮሞ ተወላጆች ተገደሉ ሕዝቡ በወንጀሉ የሚጠረጠረው ስርዓት ሁኔታውን ለጎሳ ግጭት መጠቀሚያ ለማድረግ የሚያደርገውን ቅስቀሳ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጠየቀ
13 የአለማያ ዩኒቨርስቲ የኦሮሞ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ከዓመት በላይ ታገዱ
የዛምቢያ ባለስልጣናት ሰሞኑን 19 ሲሞቱ የ75ቱን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ህይወትን ከሞት ላተረፉት የኮንጎ ድንበር ጠባቂዎች ምስጋናቸውን አቀረቡ
እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን