ሰበር ዜና ከጎንደር እና ደሴ ከተሞች

July 13, 2013

በጎንደርና በደሴ ከተሞች ለሚደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች መንግስት እውቅና ሰጠ

ነገ እሁድ ጠዋት ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም. በጎንደር እና ደሴ ከተሞች ለሚደረገው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተፈቅዶ ከፖስተር መለጠፍ፣ በራሪ ወረቀት ከመበተን በተጨማሪ በድምፅ ማጉያ ሰልፉን ያዘጋጀው አንድነት ፓርቲ ቅስቀሳውን እያደረገ ይገኛል፡፡ ይንንም ተከትሎ በተመሳሳይ ጊዜ በደሴ ከተማ አራዳ ገበያ ህንፃ አንድነት ፓርቲ ተከራይቶ ያለውን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አከራዩ እንዲያስለቅቁ ጫና ቢደረግባቸውም ፤አከራዩ አቶ መሐመድ ፓርቲው ህጋዊ በመሆኑ አላስለቅቅም፣ ህጋዊ ውል ተዋውለን ነው ያከራየሁት በሚል ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ዛሬ ሐምሌ 6 ቀን 2005ዓ.ም. የአራዳ ገበያ ህንፃ “ዕድገት አነስተኛ የሱቅ ስራ ማኀበር” ተወካዮች ነን ያሉና ስማቸውን መግለፅ ያልፈቀዱ 7 ግለሰቦች ፓርቲውን ከተከራየበት ቢሮ ለማሰለቀቅ ዛሬውኑ ከጠዋቱ 2፡30 ቃለጉባዔ ይዘው የፓርቲው የደቡብ ወሎ ዞን ጽህፈት ቤት በመምጣት ቢሮውን ባስቸኳይ ልቀቁልን ሲሉ መጠየቃቸውን ማየት ችለናል፡፡

 

Previous Story

የነፃ ሚድያ አስፈላጊነት – በኢሳት 3ኛ ዓመት (ከዶ/ር ሰይድ ሐሰን)

Next Story

ኢትዮጵያ ዛሬ ሩዋንዳን ካሸነፈች ተሳታፊ ትሆናለች

Go toTop