በአዲስ አበባ በረዶ የተቀላቀለበት ዝናብ ጥሎ በንብረት ላይ ጉዳት አስከተለ

July 10, 2013

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በአዲስ አበባ እና በአካባቢዋ በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ከስፍራው ክለዘ-ሐበሻ የመጡ መረጃዎች አመለከቱ።
በአውቶቡስ ተራ፣ በአፍንጮ በር ድልድይ እና በሌሎችም አካባቢዎች በጣለው ዝናብና በረዶ መኪናዎች እና ሰዎች ለመጓጓዝ ችግር ገጥሟቸው ሲሰተጓጎሉ ውለዋል ያሉት የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች በተለይም የንግድ ቤቶች ውስጥ እየተዝናኑ ያሉ ሰዎችን ሁሉ ውሃው ጉዳት እንዳደረሰባቸው ተናግረዋል። ምንጮቹ አክለውም ውሃው በአንዳንድ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ሳይቀር በመግባት ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ማህበረሰቡም ከቤቱ ውስጥ የገባውን ዝናብ ለማውጣት ሲታገል በአንዳንድ ሰፈሮች ታይቷል።

የዛሬውን ዝናብ ተከትሎ ጋዜጠና ገጣሚ ፋሲል ተካልኝ በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን ከፎቶ ግራፍ ጋር አስፍሯል።
____ወይ ጥጋብ!¡!____
የአፍሪካ መዲና..ውዴ አዲስ አበባ
ከባቡሩ በፊት..አሰኘሽ ወይ ጀልባ?!?
* * *
___ፋሲል ተካልኝ አደሬ___

Previous Story

«ዉጡ ፤ በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ተሳተፉ!» እስክንድር ነጋ

Next Story

ጉዳዩ የመብት እንጂ የፖለቲካ አይደለም

Go toTop