በምስራቅ ጎጃም ደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

February 9, 2016

ቀጣዩ እንደወረደ የቀረበው ዘገባ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ነው::

‹‹የትምህርት ጥራት ይጠበቅ!›› ተማሪዎች

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኘው የደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡

ምንጮቹ ዛሬ ጥር 30/2008 ዓ.ም እንደገለጹት በትምህርት ቤቱ የሰሚስተሩን አጋማሽ ረፍት ጨርሰው ተማሪዎች ወደትምህርት ቤቱ ቢመጡት መምህራኑ በስራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው ተማሪዎቹ ‹‹የትምህርት ጥራት ይጠበቅ!›› በማለት መፈክር እያሰሙ ወደቤታቸው ተመልሰዋል፡፡

የደብረ ወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ካለፈው ዓመት የካቲት ጀምሮ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ከርሟል ያሉት ምንጮቹ በዋናነት ከመመሪያ ውጭ በርዕሰ መምህርነት የሚሾሙት አካላትና የወረዳው የት/ት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍቅረአዲስ ሙሉሰው ለችግሩ መባባስ አስተዋጽኦ አላቸው ተብሏል፡፡

‹‹በክልሉ የሌለ አሰራር በመከተል በት/ቤቱ 4 ምክትል ርዕሰ መምህራን ተሹመውብን ቆይተዋል፤ ይህ መመሪያ ይጥሳል ብለን ታግለን አስወረድናቸው፡፡ ነገር ግን ከወረዱት መካከል አንዱን ርዕሰ መምህር አድርገው እንደገና ሾሙት፡፡ በዚህም ችግሩ ተባብሶ ቀጠለ፤ እኛም ድርጊቱ ትምህርትን ይጎዳል ብለን ከዛሬ ጀምሮ አድማ ልናደርግ ችለናል›› ብሏል አድማ ከመቱ መምህራን አንዱ፡፡

በት/ቤቱ 141 መምህራን እንዳሉ የጠቆሙት ምንጮቹ፣ ከእነዚህ መካከል ከ100 በላይ የሚሆኑት የአድመውን ተካፋይ ናቸው ተብሏል፡፡ የትምህርት ቤቱ አስተዳደርና የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት መምህራኑን ‹‹ሰማያዊ ፓርቲን እንጂ ኢህአዴግን አትቀበሉም›› እያለ ችግሩን ለመግፋት እየሞከረ እንደሆነም ምንጮቹ አክለው ግልጸዋል፡፡

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/12564#sthash.DNnywcVH.dpuf

Previous Story

“ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል” አሉ . . . ወይ ብሔረ-ጽጌ! – አከለው የሻነው ደሴ

Next Story

ለልጅ የሳቁለት፣ ለውሻ የሮጡለት፣ ለፖለቲከኛ ያጨበጨቡለት – ይገረም አለሙ

Go toTop