ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን)የተሰጠ መግለጫ
የወያኔ ዘረኛው ቡድን በጎንደር ቋራ አካባቢ ህዝባችንን ለመከፋፈል በሚወስደው እርምጃ ጊዜ የሚሰጠው ባለመሆኑ አፋጣኝ አጸፋዊ እርምጃ ወስደናል፡፡
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ(አዴሃን) ከተመሰረተበት ዋና አላማ አማራን ከጥፋት ለመታደግ በመሆኑ ይህ ከሰሞኑ አንድን ህዝብ በመክፈል ነጣጥሎ ለማጥቃት ሲራወጡ የነበሩ ህወሓት እና የህወሓት ቅጥረኞች ላይ እርምጃ ወስደናል።
በዘረኛው የወያኔ ቡድን በመላው ኢትዮጵያ የሚያደርሰው ማፈናቀል፡ ማጥፋት፡መግደል፡ወዘተ አልበቃ ብሎት አሁን ደግሞ ድብቅ ሴራዉን በመርዝ በመለወስ እርስ በርስ ለማፋጀት የሚያደርገው ሙከራ መቼም ቢሆን አይሳካለትም። ይህን የህውሓት የረከሰ አላማ የሚፈጽም፡የሚያስፈጽም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የተባበረ ከተጠያቂነት አይድንም።ከሰሞኑ በቋራና መተማ አካባቢ የህውሓት ባለ ሃብቶች የዚህ እኩይ ተግባር ሲፈጽሙ እና ሲያስፈጽሙ ስለተገኙ ንቅናቄያችን እርምጃ ወስዷል። አሁንም እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል:
ዛሬ በሃገራችን እንደ ሰደድ እሳት የሚቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ከኛ የጦር ተጋድሎ ጋር ተደምሮ ሲታይ የህወሓት
ውድቀት ቅርብ ጊዜ እንደሆነ መገንዘን አያዳግትም፡፡
ይሁን እንጂ ህወሓት ከመነሻው ጀምሮ ይዞት የተነሳውን ዕቅድ አማራ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡ ንቅናቄያችን ከህዝብ ጋር በመሆን ይህን ዕቅድ ያከሽፋል:: ህወሓትንም ይደመስሳል፡ብሎም ለኢትዮጵያ ነጻነት ጥግ ድረስ ይጓዛል፡፡
ዛሬ ንቅናቄያችን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ሃይሉን አጠናክሮ ህዝባችንን ለመታደግ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ነው።ይህንን ህዝብን እና አገርን ከጥፋት ለመታደግ የሚደረግን ትግል በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር የምትገኙ ኢትዮጵያዊያኖች ንቅናቄያችንን በመቀላቀልና በማንኛውም መንገድ በማገዝ ህዝባችንን ከጥፋት እንታደግ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
የአማራ ህዝብ ትግል ያሸንፋል!
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ታህሳስ 3፡2008 ዓ.ም