“በአማራ ብሄር ተወላጅ ወገኖቻችን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እየደረሰባቸው ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ኣጥብቄ እኮንናለው” አምዶም ገብረሥላሴ

November 20, 2015

ይህ ዜጎች ባገራቸው ይህ የመሰለ ጭፍጨፋ መካሄዱ እጅጉን የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ሰብኣዊነት የጎደለው ተግባር ነው።
መንግስት ለዚህ ኣስደንጋጭና ዘግናኝ ተግባር ሃላፍነት በመውሰድ ወንጀሉ በኣስቸኳይ እንዲያስቆመውና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ኣለበት እላለው።
(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)
ዜጎቻችን በስደት ሳውዲ ዓረብያ፣ የመን፣ ደቡብ ኣፍሪካ፣ ሊብያ፣ ደቡብ ሱዳንና ቤሩት የመሳሰሉ ሃገራት፤ በቀይ ባህር፣ ሜድትራንያን ባህር፣ በሲናይና ሰሃራ በረሃዎች እየደረሰባቸው ያለው መቅዘፍት ሳይበቃ በገዛ ሃገራቸው ይህን የመሰለ ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ ሊደርስባቸው ኣይገባም።

ሃገራችን 15 ማልዮን በኣስከፊ ረሃብ በያዘበትና ሂወቱ እያጣበት ባለበት ግዜ ይህን መሰል ወንጀል መፈፀሙ የሚዘገንን ብቻ ሳይሆን የሚያሳፍር ወንጀል ነው።

ብኣዴንም እወክለዋለውና ኣስተዳድረዋለው የሚለው ህዝብ ኣስከፊ ወንጀለ እየተፈፀመበት እያየ የሰው መሰውያ እንደለመደ ጣኦት ምንም ሳይል ደማቅ በዓል እያሳለፈ መሆኑ ያስገርማል።
የኢህኣዴግ መንግስትም እንደዚህ ዓይነቶች ወንጀሎች የሚፈፅሙ ወንጀለኞች ይዞ ለፍርድ የማያቀርብ ከሆነ ኣስፍኘዋለው የሚለው ሰላም ከመደፍረሱ በላይ የወንጀሉ ተባባሪና ቁጥር ኣንድ ተጠያቂ ያደርገዋል።
መንግስት ወንጀለኞች ባስቸኳይ ለህግ ያቅርብልን !

Previous Story

Hiber Radio ፡በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከተፈጥሮ ችግር ባሻገር የመልካም አስተዳደር እጦት ውጤት ጭምር መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ፣ የኢትዮጵያው አገዛዝ ስኳር ለውጭ ገበያ ላቀርብ ነው ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ፣ የግብጽ የጸጥታ ሀይሎች የበርካታ ስደተኞችን አስከሬን ከበረሃ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ገለጹ ፣ በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ በኢትዮጵያ የተከፈተበት ክስ እንዲቋረጥ ወንድሙ ጠየቀ ፣ በአገር ቤት ዜጎች በርሃብ የሚሞቱ ወገኖቻቸውን ለመርዳት በግላቸው ቤዛ እንሁን ሲሉ ኮሚቴ አቋቁመው እንቅስቃሴ ጀመሩ ፣ለርሀቡ ትኩረት አልተሰጠም በመቀሌ ለብአዴን 35ኛ ዓመት ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ተደረገ ፣ የታክሲና ሊሞ አሽከርካሪዎች ሁበርን ጨምሮ ለሌላ ኩባንያ እንዳያሽከረክሩ የሚከለክል ሕግ የለም ፣የታክሲ ኩባንያዎች ሊዝ ለመስጠት ለመስተት የሚያስችላቸው የሕግ ረቂቅ ላይ ውይይት ሊደረግ ነው እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ ጋር እና ሌሎችም አሉን

Next Story

Hiber Radio: በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እጁ ያለበት ያሸባሪዎች መሪ አሜሪካ በወሰደችው ጥቃት ሳይገደል እንዳልቀረ ተገለጸ | የሎስ አንጀለስ ፖሊስ አንድ የቀድሞ የኢትዮጵያን መኮንን አፋልጉኝ አለ | ዶ/ር ኑሩ ደደፎ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይናገራሉ | የአርበኞች ግንቦት 7 በሳን ሆሴ የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ለነጻነት ትግሉ የኢትዮጵያውያን ምላሽ | የኢትዮ-ኬኒያ ድንበር ወታደራዊ ውጥረት አይሏል፣ኢትዮጵያ የድንበር ኬላዎቿን ዘጋች… ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Go toTop