ከግንቦት 1983 ዓ.ም. አንስቶ ለቀጣይ 21 ዓመታት ኢትዮጵያን የመሩት የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሦስተኛ የሙት ዓመት ታስቧል። የሙት ዓመታቸዉን ለመዘከርም የተለያዩ ዝግጅቶች መከናወናቸዉ ተሰምቷል።
የሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደሚሉት የቀየሷቸዉ በተለይም የልማት እና የምጣኔ ሃብት መርሆዎችን ስልጣን ላይ የሚገኘዉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ እየሠራ ነዉ። ባለስልጣናቱም የእሳቸዉን ዉርስ እና ቅርስ ለማስቀጠል ቃል ሲገቡ ይደመጣል። ለመሆኑ አቶ መለስ በምን ይታወሳሉ? ዉርሳቸዉስ? ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
[jwplayer mediaid=”46290″]
Source -Deutsche Welle