የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የጥብቅና ሙያቸው ኮሚቴዎቹ የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ቀን መሰረዙ ታወቀ

July 9, 2015

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ
ሰበር ዜና ቢቢኤን
ቢቢኤን ሃምሌ 2/2007

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ጠበቃ የሆነው ጠበቃ ተማም አባቡልጉ በፍርድ ቤት ላይ በሚያደርጋቸው ክርክሮች በተለይም መንግስት ከጅሃዳዊ ሀረካት ጀምሮ የሰራቸውን ሸፍጦችና ኢትዪጲያዊ ውስጥ የፍትህ ስርአቱን ዝቅጠት በመረጃና በህግ በማጣቀስ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በማጋለጣቸው ምክኒያት ከዚህ ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ማስፈራሪያና ዛቻዎች ከመፈጸማቸውን ሌላ እብድ በሚመስል ሰው በመላክ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ይታወቃል፡፡

ይህ ሁሉ ግፍ ተፈጽሞባቸው በጀግንነት ከስራቸው ያልቆሙት እንዲሁም የህግ ክፍተቶችን ጭምር በማጋለጥ፤ ከኮሚቴዎቹ በተጨማሪ መንግስት የከሰሳቸው የነ አብራ ደስታ ጠበቃ የነበሩትን ተማም አባቡልጉን መንግስት በኮሚቴው ላይ የጥፋተኝነት ብይን ባስተላለፈበት እለት የጥብቅና ሙያቸውን ፍቃድ ፍትህ ሚኒስትር መሰዘረዙ ታውቋል፡፡
አቶ ተማም አባቡልጉ ያለ ምንም ፍርሃት እውነታውን በሚዲያዎች ላይ በማጋለጥ ታላቅ አስተዋጾ ያበረከቱ፤ በብዙዎች ዘንድ በጀግንነት የሚጠሩ ፤ ፤ለሙያቸው ያደሩ ጠበቃ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ቢቢኤን ጠበቃ ተማም አባቡልጉን በማነጋገር ተጨማሪ መረጃ ይዞ የሚቀርብ ይሆናል::

Previous Story

በአፋር ክልል ወጣቶች ለውትድርና በግዴታ እየታፈሱ ነው

Next Story

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የሚታየውን ውጥረት ተከትሎ አየር ሃይል በጠንቀቅ እንዲቆም ታዘዘ

Go toTop