ጎሳዬ ቀለሙን ምን ነካው ?

June 23, 2015

ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
እዚህ ሀገር ድንገት ተነስተው አየር ምድሩን ሁሉ መሙላት የሚፈልጉ አሉ ። ቢችሉ እሰየው ። ግን ክፋቱ ደግሞ ሀገሪቱ ለዚህ አትመችም ። በወጡበትየሚጨብጡ የሚረግጡትን አጥተው በወጡበት ፍጥነት ሲወርዱ አይተናል ። ድምፃዊ ጎሳዬ ቀለሙም ከእነዚህ አንዱ እንዳይሆን እሰጋለሁ ። በግሌ እንደነ አብርሀም አፈወርቂ ፣ ሄለን መለስ ፣ የማነ ባሪያ ለመሳሰሉት የኤርትራ ድምፃውያን (ለድምፃቸው) ያለኝ አክብሮትና ፍቅር ከኤርትራውያኑ የሚያንስ አይመስለኝም ። እዚህ ሀገር ያሉ የኛ ድምፃውያን የኤርትራውያኑን ተወዳጅ ስራዎች አምጥተው ሲጫወቱባቸው ( እነሱ ዘፈንን ነው የሚሉት) በእጅጉ እበሽቃለሁ ። የአብርሀም አፈወርቂን ዘፈኖች ከነጎሳዬ ጥቃት ለመከላከል ኤርትራዊ መሆን ወይም ቋንቋውን ማወቅ ግዴታ አይደለም ።ጎሳዬም የአብርሀም አፈወርቂን ” መለይ” የተባለ ዘፈን (የፍቃድ ነገር መቸም አይነሳም) ወስዶ መዝፈኑ ሳያንስ ያለፍቃድ የዘፈነውን ዘፈን ይዞ ” የሌባ አይነ ደረቅ ” እንዲሉ “አስመራ ሄዶ በመዝፈን የመጀመሪያው” ለመሆን መመኘቱ ዘ ይገርም ነው ። ወዳጆቹ ካላችሁ አብርሀምን የበላ የኤርትራ ባህር ዳርቻ አሸዋ ውጦ እንዳያስቀረው ብትመክሩት ይበጀዋል ። ለነገሩ እዚያ የሚያደርሰውም አይኖርም ። ልጁ ግን ምን ነካው ?

Previous Story

የሰላም ትግሉ በኢትዮጵያ (ክፍል ፩) – አንዱዓለም ተፈራ

Next Story

ከገዥው ወገን የምንለይበት፤ አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘገጅ

Go toTop