(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ በአይሲኤል የተገደሉትን 28 ኢትዮጵያውያን ለማሰብ በተጠራው የፍትሃት ስነ-ስርዓት ላይ ከኢትዮጵያውያኑ ከ20 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ታወቀ::
የቤተክርስቲያኑ አስተዳደር ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ እንዳስታወቀው ይህ እርዳታ የመጀመሪያው እንጂ የመጨረሻው አይደለም:: እንደ አስተዳደሩ ገለጻ ትናንት እሁድ በቤተክርስቲያኑ በተደረገው የፍትሃትና የጸሎት ስነስርዓት ላይ ሕዝቡ ሃዘኑን በሰፊው የገለጸ ሲሆን በሊቢያ በስቃይ ላሉ ኢትዮጵያውያን መርጃ የሚሆን ከ20 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡን አስታውቋል::