መኢአድ ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ሊያደርግ ነው

October 12, 2014

ለተቃውሞ ሰልፉ ህዝቡ እንዲዘጋጅ ጥሪውን አቅርቧል።

በነገው ቀን ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት የተቃውሞ ሰልፉን ቀን ይፋ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቀው መኢአድ በፋሽሽቱ ወያኔ በጋምቤላ በጉራፈርዳ እና በሱማሌ ክልል እየተካሄደ ያለዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል በጋራ ለማስቆም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሳተፍበት ተከታታይ የተቃዉሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ይደረጋል ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አስታወቀ።

“በዉጭም በሃገር ዉስጥም የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ከጎናችን በመቆም ይህን ዘረኛ ስርዓት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በዲሞክራሳዊ ስርዓት እንቀይረዉ” ያለው መኢአድ አስፈላጊዉን ዝግጅት ሁሉ ማጠናቀቁን ገልጾ ለተቃውሞ ሰልፉ ህዝቡ እንዲዘጋጅ ጥሪውን አቅርቧል።

Previous Story

በአፋር ክልል አሳዛኝ የጎርፍ አደጋ ደረሰ

Next Story

Hiber Radio: በአሜሪካ አንድ ሐበሻ ኢቦላ ይኖረዋል በሚል ተጠርጥሮ ተያዘ፤ ኢቦላ አለብኝ ብሎ የቀለደው አሜሪካዊ ከአውሮፕላን ለመውረድ ተገደደ

Go toTop