ፀረሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን የሀብት ዝርዝር ላለማሳወቅ እያንገራገረ ነው

May 23, 2013

ፍኖተ ነፃነት

የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣኖችን የሀብት በዝርዝር ይፋ ለማድረግ ማመንታቱ በፓርላማ መነጋገሪያ ሆነ፡፡

የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ባለፈው ሳምንት ግንቦት 6 ቀን 2005 ዓ.ም ለፓርላማ ባቀረቡት የ2005 በጀት የአስር ወር የዕቅድ አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት በዝርዝር ይፋ ለማድረግ ማመንታታቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ኮሚሽነሩ ባለፈው አመትም ተመሳሳይ ሪፖርት ሲያቀርቡ “በቅርቡ የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት በዝርዝር ይፋ እናደርጋለን” ቢሉም በያዝነው አመትም ይፋ አለመደረጉ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ኮሚሽነሩ ሲመልሱም በአስደንጋጭ ሁኔታ “የሚገለፅና የማይገለፅ አለው” ብለዋል፡፡
ብቸኛው የተቃዋሚ ወኪል የሆኑ አቶ ግርማ ሰይፉ “የተሽዋሚዎች ሀብት የሚገለጽና የማይገለፀው ምንድነው?” የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም በቂ ምሳሽ እንዳላገኙ ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡ ጨምረውም “ፀረ ሙስና ኮሚሽን አሁንም የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብትና መረጃ ይፋ ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ መውሰድ የለበትም” ካሉ በኋላ፣ ባለስልጣናቱን በሚመለከት የሚገለፅና የማይገለፅ መረጃ ሊኖር እንደማይገባ አሳስበዋል፡፡

Previous Story

ሕገ ወጥነት ከዓላማችን አይገታንም!!! (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማብራሪያ)

Next Story

የባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበር ከፍተኛ አመራር ታሰረ

Go toTop