ፓትርያሪክ መርቆርዮስ ለምን እንደተሰደዱ ምላሽ የሚሰጥ ባለ 63 ገጽ መጽሐፍ ታትሞ ወጣ (ይዘነዋል)

May 23, 2013

(ዘ-ሐበሻ) ማርች 5 ቀን 2013 በአዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ “ቤተክህነታዊ ሃረካት” ሲሉ ምእመናን የተቹትን ባለ 52 ገጽ መጽሐፍ በስደተኛው ሲኖዶስ ዙሪያ አሳትሞ መበተኑን በወቅቱ ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም። በስደት የሚገኘው ሲኖዶስም ለዚህ መጽሐፍ ምላሽ የሆነ ባለ 63 ገጽ ትንሽ መጽሐፍ አሳትሞ በትኗል። ይህ መጽሐፍ በኢሜይል፣ በድረ ገጽ እንዲሁም ታትሞ እየተሠራጨ ሲሆን አቡነ መርቆርዮስ ለምን ሊሰደዱ እንደቻሉና እንዴት እንደተሰደዱ? ለቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊና ታምራት ላይኔ ጽፈዋቸው የነበሩ ደብዳቤዎች፣ እንዲሁም ሕወሓት በበርሃ በነበረበት ወቅት ለሰላም እንዲሰሩ የጻፏቸውን ደብዳቤዎች ሁሉ ይዟል።

በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ይህን ለአዲስ አበባው ሲኖዶስ ላሳተመው “ቤተክህነታዊ ሃረካት” ምላሽ የሚሆን መጽሐፍ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች እንዲያነቡት ልኮልናል እንደሚከተለው አስተናግደነዋል።

መጽሐፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (PDF)

Previous Story

አቡነ ሕዝቅኤል የ6ኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ድጋፍ ነፍገውኛል ያሏቸውን እየተበቀሉ የሚያስመስል ድርጊት እየፈጸሙ ነው ተባለ

Next Story

ሕገ ወጥነት ከዓላማችን አይገታንም!!! (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማብራሪያ)

Go toTop