የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት 400 ሰዎች በተገደሉበት የጋምቤላ ጭፍጨፋ የሕወሓት ባለስልጣናት መሳተፋቸውን አጋለጡ

September 9, 2014

የቀድሞው የጋምቤላ መሪ በክልሉ ለደረሰው ጭፍጨፋ የህወሃት ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረጋቸውን ኢሳት ዘገበ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ኦሞት ኦባንግ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ 400 ሰዎች የተገደሉበት የጋምቤላው ጭፍጨፋ እንዴት እንደተከናወነ በዝርዝር ሁሉን ነገር ተናግረዋል።

እንደ ኦሞት ገለጻ የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አባይ ፀሐዬ ግድያውን በተመለከተ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ያሉ ሲሆን በክልሉ ስለሚፈጸመው ሙስናና የመሬት ወረራ የቀድሞው ባለስልጣን በዝርዝር በዝርዝር ተናግረዋል።

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦሞድ ወደ ውጭ ከወጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሰጡት በተነገረው በዚህ ቃለምልልሳቸው ላይ 400 ሰዎች በግፍ በአባይ ፀሐዬ ከፍተኛ ሚና መገደላቸውን መዘርዘራቸው ወደፊት በነዚህ ባለስልጣናት ላይ ለሚከፈተው ክስ ጥሩ ምስክር ሊሆን ይችላል ተብሏል።

Previous Story

Hiber Radio: በአንዋር መስጊድ ያለ ሀባሽ ፈቃድ ሃይማኖታዊ ትምህርት መስጠት የሚከለክል መመሪያ ወጣ፤ በጅጅጋ የክልሉ ታጣቂዎች ኦብነግን ተቀላቀሉ

Next Story

ኢህአዴግ የመልካም አስተዳደር ችግር በማንም የማይላከክ ነው አለ

Go toTop