የዘ-ሐበሻ አንባቢያን የዓመቱ ምርጥ ሰው – (ድምጽዎን አሁኑኑ ይስጡን)

August 17, 2014

ዕውነት ያሸንፋል! የሚለውን መርህ አስቀድማ ወቅታዊ መረጃዎችን ለሕዝብ የማድረስ የ7ኛ ዓመት ጉዞዋን የጀመረችው ዘ-ሐበሻ በየዓመቱ አንባቢዎቿን በማሳተፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በዓመቱ ትልቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን “የዓመቱ ምርጥ ሰው” በማለት ትሰይማለች። ባለፈው 2005 የኢትዮጵያውያን ዘመን የዓመቱ የዘ-ሐበሻ አንባቢያን ምርጥ ሰው ተብሎ የተሰየመው በእስር ላይ የሚገኘው አንዷለም አራጌ ነበር። ዘንድሮም እንዲሁ የ2006 የዓመቱ ምርጥ ሰው ምርጫዎን በየትኛውም ዘርፍ በኢትዮጵያ በዓመቱ ትልቅ ሥራ ሰርቷል የሚሉትን ሰው እንዲመርጡ አንባቢዎቿን ዘ-ሐበሻ ትጠይቃለች።

የዚህን ምርጫ ውጤት ዘ-ሐበሻ ጷጉሜ 2006 ዓ.ም ለአንባቢዎቿ ታቀርባለች።

ምርጫዎን፡ በአስተያየት መስጫ ሳጥን፣ በኢሜይል

info@ethiopoint.com
admin@ethiopoint.com

በስልክ ቁጥር

 612 – 986 0557

ላይ መደወል ወይም ቴክስት በመላክ፣ ልታሳውቁን ትችላላችሁ።

 

 

Previous Story

ግልፅ ደብዳቤ ለአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አባላት (አሰፋ ዘለቀ)

Next Story

ትክክል! (ሥርጉተ ሥላሴ)

Go toTop