የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ማዕከላዊ እንዲቀርብ ታዘዘ

May 23, 2014

በየ15 ቀኑ ለንባብ በምትቀርበው ዕንቁ መጽሔት በዋና አዘጋጅነት ይሰራ የነበረው ጋዜጠኛና ደራሲ ኤልያስ ገብሩ በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ እንዲቀርብ መታዘዙን ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
ኤልያስ ገብሩ በማዕከላዊ ቃሉን እንዲሰጥ የታዘዘው ከመጽሔቱ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ቢታወቅም በየትኛው ወር ወይም አመት በቀረበ የዕንቁ ህትመት እንደሆነ አልታወቀም፡፡ጋዜጠኛው ከመጽሔት ዋና አዘጋጅነት በተጨማሪ የሳይኮሎጂና ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት የተሰኙ መጻህፍትን ለንባብ ማብቃቱ ይታወቃል፡፡
Source: Dawit Solomon

Previous Story

አንድነት በአዳማ ከተማ የጠራው ሰልፍ ለሰኔ አንድ መተላለፉን አስታወቀ

Next Story

በሕግ አምላክ! የኢትዮጵያን ታሪክ የቆነፀላችሁበት እና ያደበዘዛቹበት አቀራረብ ይስተካከል።የመንግስት የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ድረ-ገፅን ይመለከታል።

Go toTop