(ሰበር ዜና) በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ እሳት ቃጠሎ ተነሳ

May 21, 2014

(ዘ-ሐበሻ) የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ የመረጃ ምንጮች እንደጠቆሙት በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ አካባቢ የሚገኘው ኒውዮርክ ካፌ አጠገብ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ማጥፊያ ማርሻል አካባቢው የደረሰ ሲሆን እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ መረጃዎች ደርሰውናል:።

ዛሬ ቀትር ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ያልጠፋ ሲሆን እሳት አደጋ ሰራተኞች ግን ርብርቦሻቸውን ቀጥለዋል። የእሳት አደጋው መነሻ ምን እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም።

Previous Story

ሄኖክ የሺጥላ – (አምቦ ተነሽ አትነሺ)

Next Story

“በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ የሚፈጠሩ ናቸው” አርቲስት መኮንን ላዕከ

Go toTop