Hiber Radio: ለኢትዮጵያ ይሰልላል የተባለ ሱማሊያዊን አልሸባብ ገደለ፤ * በአሶሳ የተገደሉ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን አስከሬን መቀሌ ገባ

May 19, 2014

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ግንቦት 10 ቀን 2006 ፕሮግራም
<<...ስርዓቱ በዘር ሊያጋጭ ይሰራል። ጎሳን ማክበር ጥሩ ነው ግን ከጎሳም፣ ከሀይማኖትም በፊት ሰው ነን። ኢትዮጵያውያን ከጎሳ ይልቅ ለሰውነታችን ቅድሚያ ሰጥተን ይህን ስርዓት በአንድ ላይ መታገል አለብን ...>>

አቶ ኦባንግ ሜቶ የትብብር ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር በወቅታዊ ጉዳይ ለህብር ከሰጡት ኢንተርቪው የተወሰደ

<...ኢትዮጵያውያን በአገራቸው በየትኛውም ክልል መኖር መብታቸው ነው ። ይሄ ጎሳን ከጎሳ ለማጋጨት መሞከርን በገዢው ፓርቲም ሆነ በሌሎች የሚደረገውን መድረክ አይቀበለውም...>

አቶ ጥላሁን እንደሻው የመድረክ ስራ አስፈጻሚ አባል ለህብር ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ

ሱዳንና ክርስቲያን በመሆኗ ሞት በፈረደችባት ኢትዮጵያዊት ሳቢያ እየደረሰባት ያለው ዓለም አቀፍ ተቃውሞ (ልየ ዘገባ)

<<... አገር ቤት ለመላክ የሰጠነው ዕቃ ለወራት ተጉላልቶ አሁን ደግሞ አዲስ መመሪያ ወጣ ብለው አግደውብናል...የት እንደምንሄድ አናውቅም ብዙዎች ዕቃችን ይመጣል ብለው አገር ከገቡ በሁዋላ የለፉበት ንብረት እዚሁ ቀርቷል። ለማን አቤት እንላለን?...>>

በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት በሚልኩት እቃ ላይ በአየር መንገድ የተጣለባቸው እገዳ ጉዳት እያደረሰባቸው እንዳለ ቃለ መጠይቅ የሰጠችን ኢትዮጵያዊት ምስክርነት(ያዳምጡት)

ከሀይለማርያም ጀርባ ያለው የህወሃት ጠንካራ እጅና የገቡበት አጣብቂኝ ..ባለስልጣኑ ማነው? (ልዩ ዘገባ)

ዜናዎቻችን

* አቶ ኦባንግ ሜቶ ኢትዮጵያውያን ከጎሳ ይልቅ ለሰውነት ቅድሚያ ሰጥተው ነጻነት ለማግኘት በአንድ ላይ እንዲታገሉ ጠየቁ

* በአሶሳ የተገደሉ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን አስከሬን መቀሌ ገባ

– አገዛዙ ከሐዘን ይልቅ የሙዚቃ ድግስ ማድረጉም ተገለጸ

* ለኢትዮጵያ አንድ መርከብ የተሰጠው ስያሜ ቅሬታ ፈጠረ

– ድርጊቱ የስርዓቱን ከፋፋይነት ያጋልጣል ተብሏል

* የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ባልዳዊ ከተማ ነቅሎ ወጣ

* ለኢትዮጵያ ይሰልላል የተባለ ሱማሊያዊን አልሸባብ ገደለ

* ኤርትራውያን በአገራቸው ላለ ጭቆና የፈጣሪን ጣልቃ ገብነት እንሻለን ብለው አደባባይ ሰልፍ ሊወጡ ነው

* ግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሀይል አራተኛ ዙር ሰልጣኖችን አስመረቅሁ አለ

* የታሰሩት የዞን ዘጠኝ አባላት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

– የተለያየ የቀጠሮ ውሳኔ ተሰጠ

* ኢትዮጵያዊው ቡጢኛ ሳሚ ረታ የግብጽ አቻውን አዲስ አበባ ላይ ሊገጥም ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Previous Story

ዘር ማጥራት ወይስ ኢህአዴግን ማፍረስ ? (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )

Next Story

ካሁን ቀደም በነፃ ከተለቀቁት ሙስሊሞች ውስጥ 2ቱ እንደገና እንዲከላከሉ ተወሰነ

Go toTop