መታሰቢያነቱ በግፍ ለተገደሉ የዮኒቨርቲ ተማሪወች።

ብርሀን አህመድ

       መንገድ ላይ ቀረሁ!!
የልቤን፣አውጥቸ__ ሳልናገር፣ለስው፣
አድካሚ፣ጉዞየን__ ሄጀ፣ሳልጨርሰው፣
እንዳሻኝ፣እንደልብ__ ሳልፅፍ፣ሳይነበብ፣
በቡቃያኔቴ__ አፍርቸ ሳላብብ።

ተምሪ፣ጨርሸ__ ሀገሬን፣ሳልጠቅም
አግብቸ፣ወልጀ__ ልጅ፣አቅፊ፣ሳልሰም፣

እናቴን፣ሳልጦራት__ አባቴን፣ሳልረዳ
አምሮብኝ፣፣ሳልታይ__ ወጥቸ፣ከጋዳ
አናቴ ላይ ጥይት __ ጉኔን፣ሰለት ወግቶተኝ
በወጣትነቴ መንገድ ላይ ቀ  ረ ሁ  መሪ።

Previous Story

Video: የእሪታ ቀን፡- ይህ ቪዲዮ ከአንድነት ሰልፍ የተቀነጨበ ሲሆን ሙሉውን ቪዲዮ ከሰዓታት በኋላ እንለቃለን

Next Story

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በደምቢዶሎ ከተማ ሕዝብ ላነሳው ጥያቄ የመንግስት ምላሽ ጥይት ሆነ፤ ውጥረቱ ቀጥሏል

Go toTop