ሰበር ዜና- የቀድሞው የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃምን ጨምሮ ታዋቂ ፖለቲከኞችና ምሁራን አንድነት ፓርቲን ተቀላቀሉ

April 30, 2014

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

አቶ አስራት አብርሃም

የቀድሞው የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃምን ጨምሮ ታዋቂ ፖለቲከኞችና ምሁራን አንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸውን አንድ አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ከፍተኛ አመራሩ ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ታዋቂው ወጣት ፖለቲከኛና ደራሲ አቶ አስራት አብርሃ እና ሌሎች በርካታ ወጣት ምሁራን አንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸው ፓርቲው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እያገኘ ያለውን ተቀባይነት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ አቶ አስራት አብርሃም በቅርቡ በአንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸውን በልዩ መርሀግብር ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ በሂደት አንድነትን እየተቀላቀሉ ያሉ የሌሎች ታዋቂ ፖለቲከኞችና ምሁራን ስም ይፋ እንደሚደረግም ከፍተኛ አመራሩ ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡ አቶ አስራት አብርሃም “ከሀገር በስተጀርባ”፣ “መለስና ግብፅ” ፣ “ፍኖተ ቃዬል” የሚሉና ሌሎች መጽሓፍትን የጻፉ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

 

Previous Story

በሰፊው የኦሮሞ ህዝብ እና ልጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ በአጽንኦት እናወግዛለን!!!

Next Story

አንድነት ፓርቲ እሁድሚያዝያ 26 ቀን 2006ዓ.ም “የእሪታ ቀን በሚል” መሪ ቃል ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬም የተጠናከረ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው፡፡

Go toTop