የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ሰልፉ እውቅና እንደተሰጠው የገለጸበት ቅጽ – ፖሊስ ቀስቃሾቹን እያሰረ ነው

April 24, 2014

ፖሊስ ቀስቃሾቹን እያሰረ ነው

ፖሊስ የእውቅናው ደብዳቤ አልደረሰኝም በሚል በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ቅስቀሳ ላይ የተሰማሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እያሰረ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በየካ፣ ካሳንቺስና አቧሬ ሲቀሰቅሱ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡ ቀስቃሾቹ ሰልፉ እውቅና እንደተሰጠው የሚያመለክተውን ወረቀት ለፖሊስ ቢያሳዩም ፖሊሶች የእውቅናው ደብዳቡ አልደረሰንም በሚል አስረዋቸዋል፡፡ ቀስቃሾቹ የያዙት የእውቅና ደብዳቤ ግልባጭ ለፖሊስ የተጻፈበት በመሆኑ ሰልፉ እውቅና አግኝቶ እያለ ሆን ተብሎ ለማደናቀፍ እንደሆነ ምክትር ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ገልፀዋል፡፡

በላም በረት፣ ቦሌ ድልድይ፣ ኮተቤ፣ መገናኛ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ቅስቀሳቸውን በተሳካ መልኩ አጠናቀዋል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች የተሰማሩት አባላት ቅስቀሳውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በሌላ በኩል በየካ፣ ካሳንቺስና አቧሬን ጨምሮ በሌሎች የከተማይቱ ክፍሎች ፖሊስ ከ20 በላይ አባላትን ማሰሩ ታውቋል፡፡

ሰበር ዜና ፖሊስ ቅስቀሳው ላይ ያልነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንም እያሰረ ነው፡፡ የታሰሩትን አባላትና ደጋፊዎች ሁኔታ ለማጣራት ወደ የካ ፖሊስ ጣቢያ ያቀኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ፖሊስ አስሯቸዋል፡፡
በዛሬው ቀን ካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት
1.      ብሌን መስፍን
2.      አስናቀ በቀለ
3.      መስፍን
4.      ተስፋዬ አሻግሬ
5.      እዮብ ማሞ
6.      ኩራባቸው
7.      ተዋቸው ዳምጤ
የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች
1.      ፍቅረ ማሪያም አስማማው
2.      እያስፔድ ተስፋዬ
3.      ጋሻው መርሻ
4.      ተስፋዬ መርኔ
5.      ሀብታሜ ደመቀ
6.      ዘሪሁን ተስፋዬ
7.      ጌታነህ ባልቻ
8.      ንግስት ወንዲፍራው
9.      ሜሪን አለማየሁ ናቸው

 

Previous Story

የሰማያዊ ፓርቲ አባል በሙስሊምነቱ ተከሰሰ

Next Story

የወታደራዊ መኮነኖች ቅነሳ?! ህወሓት እየተዳከመ መሆኑ የሚያሳይ ሌላ ማስረጃ ደግሞ በተለያዩ ክልሎች ይሰሩ የነበሩ የህወሓት የደህንነት ሰዎች ከያንዳንዱ ክልል መባረራቸው ነው!

Go toTop