ማክሰኞ ሚያዝያ 14/2006 ዓ.ም ሚያዝያ 19 ለሚደረገው ቅስቀሳ ላይ የተሳተፈው ጀሚል ሽኩር አብረውት ከታሰሩት በተጨማሪ ሌላ ክስ ተመሰረተበት፡፡ በካሳንቺስ መስመር ሲቀሰቅስ ተይዘው የታሰሩት ወጣቶች ‹‹ያልተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ›› በሚል የተከሰሱ ሲሆን ጀሚል ከዚህ ክስ በተጨማሪ ‹‹ድብቅ አላማ ለማሳካት›› የሚል ተጨማሪ ክስ ተከፍቶበታል፡፡ ይህኛው ክስ የተመሰረተበትም ከእምነቱ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ከሰማያዊ ፓርቲ ተጨማሪ መረጃ ካገኘን እንመለሳለን።