አቡነ ዳንኤልየሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ መሥራች አባት አቡነ ዳንኤል ለሰላም እና ለአንድነት ከቆሙት ምዕመናን ጋር ተነጋገሩ። አቡነ ዘካሪያስ አውግዣቸዋለሁ ያሏቸውን አራቱን የደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ካህናትን በተመለከተም “ተናደው ያደረጉት ነገር ይሆናል እንጂ ተመካክረን የምንፈታው ነው” ብለዋል። ለሰላምና ለአንድነት የቆሙት ም እመናን እንዳስታወቁት “ብጹእ አባታችን አቡነ ዳንኤል የአቡነ ዘካሪያስን በደብረ ሰላም ሜኒያፖሊስ መድሃኒያለም የማይገባ ውግዘት የወፍ ግዝትና ምንም ሃይማኖታዊ ትርጉም የሌለው መሆኑን በድምጻቸው ገልጸውልናል። ይህንን የብጹህ አባታችን አቡነ ዳንኤል የድምጽ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።” ብሏል። ድምጹን ያዳምጡ።