ቫን ኒስቴልሮይ ማላጋ ገባ

June 13, 2011

የቀድሞው የማን.ዩናይትድ ሱፐር ስታር አጥቂ ሩድ ቫንኒስተርልሮይ ወደ ሪያል ማድሪድ ተዘዋዋውሮ የነበረ ቢሆንም እዛም የተሻለ ሕይወትን ሳያሳልፍ ቀርቶ በጊዜ ወደ ጀርመኑ ሃምቡርግ ተዘዋወሮ ነበር።
በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ሳይቀር ወደ እንግሊዙ ሰንደርላንድ ክለብ ይዘዋወራል ተብሎ የነበረው ሆላንዳዊው ጎል አዳኝ አሁን የአንድ ዓመት ኮንትራት ለመፈረም የተስማማው ከስፔኑ ማላጋ ክለብ ጋር ነው። ጁላይ 1 የ35ኛ ዓመት ልደት በዓሉን የሚያከብረው ቫንኒስተልሮይ
ለማን.ዩናይትድ 150 ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ (95) ጎሎችን ለሪያል ማድሪድ 68 ጨዋታዎች 46፤ ለሃምቡርግ ከ35 ጨዋታ 12ጎሎችን ሲያገባ፤ ለሆላንድ ብሄራዊ ቡድንም 70 ጨዋታዎችን አድርጎ 35ቱ ላይ ጎል በማግባት አዳኝነቱን አሳይቷል።
ቫንኒስተልሮይ በስፔኑ ማላጋ ለአንድ አመት ያህል ይቆያል።

Previous Story

Open Letter to Hillary Clinton from Ethiopia: By Eskinder Nega

Next Story

Clinton Warns African Leaders: Reform or Face Uprisings

Go toTop